መፈንቅለ መንግስቱን ለማክሸፍ የተደረገ እንቅስቃሴ

Wednesday, 05 July 2017 12:32

 

በዚሁ ዕለት ግንቦት 8 ቀን 1980 ዓ.ም የሞቱትን ወታደሮች ለመቅበር ወደ አቦ ቤተክርስቲያን ጦሩ በብዛት ሄዶ ነበር። እኔም ቀብር ላይ ለመገኘት ስወጣ በር ላይ ፖሊስ አስቁሞ ጓድ መንግስቱ ገመቹ ቢሮ ትፈልጋለህ አለኝ። እኔም ተመልሼ ወደ ጓድ መንግስቱ ገመቹ ቢሮ ሄድኩ። ስደርስ ከቢሮ ውጭ ነው የጠበቀኝ፤ ደረስኩ። ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ በመከላከያ ሚኒስቴር ስለተጀመረው መፈንቅለ መንግስት ከነገረኝ በኋላ የምትፈልገውን ያህል ጦር ይዘህ ወርደህ እንዲከበቡ አድርግ አለኝ። ትዕዛዙን ተቀብዬ ለጦር ክፍሎች ሁሉ ትዕዛዝ ባስተላልፍ አዛዦችም አብዛኛው ጦርና የመሳሪያ የታንክ ምድብተኞች በግምት አንድ ሻምበል ያህል፣ 3 ከባድ ታንኮች፣ 3 ብረት ለበስ አዘጋጅቼ ጉዞ ጀመርን። ከእኔ ቀድመው በቶዮታ መኪናዎች መንግስቱ ገመቹና አንድ መቶ የሚሆኑ አጃቢ ወታደሮች ይዘው ከኛ ቀድመው ከመከላከያ ሚኒስቴር ምዕራብ ከንግድ ባንኩ ፊት ለፊት እንደደረሱ መከላከያ ሚኒስቴሩ ከቢሮ ለመውጣት ሲጣደፉ ኮለኔል አበራ የተባለው ተመልክቷቸው ኖሮ ተከታትለው ሊወጡ በር ላይ እንደደረሱ በሽጉጥ ጥይት ተኩሶ ይመቷቸዋል። በሱም ላይ አጃቢ ወታደሮች ይተኩስበታል። ወደቀኝ እጥፍ ብሎ በመከላከያ ቢሮ ሰሜት አንድ ፎቅ አለ በመከላከያ ቢሮና በፎቁ መካከል ያለው አጥር በባህርዛፍ እንጨት የታጠረ ነበር። ኮለኔል አበራ በዚያ ዘሎ ፎቁ ውስጥ ይገባና በያዘው ሽጉጥ አስፈራርቶ የአንድ ዘበኛ ልብሱን አስወልቆ የራሱ የማዕረግ ልብሱን ከዘበኛው ቤት ጥሎ የዘበኛውን ልብስ ለብሶ በጦሩ መሃል ሲያልፍ አልተነቃበትም። ፎቁ እራሱ ከአካባቢው ጥበቃ ስር ነበር። መከላከያ ዙሪያውን ተከበበ። የፖሊስ ዋና አዛዥ ጀነራል ወርቁ ከተስብሳቢ መኮንኖች አንድ ናቸው። ከስብሰባው ወጥተው ጓድ መንግስቱን ሰላዩ እኔ ሳላውቅ ነው ለስብሰባ ትፈልጋህ፤ ብለው ያስገቡኝ እባክህ እንድወጣ ፍቀድልኝ አሉት። ይቆዩ አላቸው በመከላከያ ጸጥታ ሰፈነ። ሰው ሁሉ የፎቁን መስታወት መጋረጃ እየገለጠ ይመለከታል። ዙሪያውን በታንክና በእግረኛ ጦር ተከበዋል። (ገፅ፤ 104)

                                                                             (ምንጭ- ከአባ ኮ/ሽፈራው “በምጥ ተወልዶ በምጥ ያደገ” መጽሐፍ የተወሰደ)

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
356 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 910 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us