ተስፋ እንደ ምትሐት

Thursday, 13 July 2017 14:30

 

ነጋ

 

 

የግዜር ስውር  መዳፍ

ልክ እንደፓፒረስ፣ እንደግብጦች መጣፍ

ወይም እንደጥንቱ፣ ያበጅፋር ምንጣፍ

ጨለማውን ስቦ፣ በወግ ሸበለለ

ሰማይ የጠፈር ዓይን፣ ብርሃን ተኳለ

ከዶሮ ጩኸት ውስጥ፣ አዲስ ጎሕ ተወልዶ

ፍጥረቱ በሙሉ፣ ማርያም ማርያም አለ፤

 

ነጋ

 

 

አልጋየን ሰብሬ

አንሶላ ተርትሬ

ባዲሱ ጉልበቴ

በታደሰ አሞቴ

ልኖር ተዘጋጀሁ

እንደጣዝማ ቅንጣት

ከሚጣፍጥ ሞቴ

ትንሳኤየን ዋጀሁ፤

 

ነጋ

 

እንደምትሐተኛ፣ ተስፋ ሲያታልለኝ

አዲሱ ማለዳ፣ “ዛሬን ሞክር” ሲለኝ

የዛሬው እጣየ

ከትናንት ጣጣየ

የሚለይ መሰለኝ።

(“የማለዳ ድባብ” - ከተሰኘው አዲሱ የበዕውቀቱ ሥዩም የግጥም መድብል የተወሰደ)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
268 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 757 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us