የኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ የህይወት ፍፃሜ ድራማ

Thursday, 13 July 2017 14:31

 

“ፍትሃዊ የሆነ ፖለቲካዊ ስርዓትን በማስፈን የሕዝቦች እኩልነትን ማረጋገጥ ይቻላል” በሚል የትግል መርሁ ከአርጀንቲና ተነስቶ እንደ ኩባ፣ ራሺያ፣ ኮንጎ፣ ቦሎቪያና ፔሩ ወደ መሳሰሉት አገራት በመጓዝ ጭቁን ሕዝቦችን ከአምባገነንና ጨቋኝ የውስጥና የውጭ ቅኝ ገዥ ኃይሎች ነፃ ለማውጣት እስከመጨረሻው ድረስ በፅናት በመፋለም የሕዝብ ወገንተኝነቱንና ድንበር ዘለል የነጻነት ተጋዳይነቱን በተግባር አረጋግጧል።

ጉቬራ ዛሬም ድረስ በተለይ በላቲን አሜሪካ የፍትህ፣ የዲሞክራሲና የሶሻያሊስት ስርዓት አቀጣጣይ ፖለቲካዊ ኃይል እንደሆነ የመቀጠሉ እውነታ በገሀድ እየታየ ይገኛል። ይኼም ቦሊቪያን፣ ቬንዙዌላን፣ ኢኳዶርን፣ ኒካራጉዋን፣ ብራዚልን፣ ሜክሲኮንና የመሳሰሉትን አገራት ባጥለቀለቀው የፀረ አሜሪካ ካፒታሊዝም የተቃውሞ ማዕበል የተረጋገጠ ሀቅ ነው። ከግራ ዘመም ኃይሎች ጋር የተጋራው ሕልሙም ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በሰፈነባቸው የላቲን አገራት እውን ሊሆን ችሏል። ይህ የለውጥ ማዕበል በሂደት እንደ ካምቦዲያ፣ ፔሩና ጓቲማላ የመሳሰሉትን አገሮችም አዳርሶ አልፏል። ቼ ጉቬራ በ1967 ዓ.ም የካፒታስት ኃይሎች ካሰማራቸው ታጣቂዎች በተተኮሰበት ጥይት የተገደለ ሲሆን በሞተበት ወቅት በመላው ዓለም የሚገኙ ተከታዮቹና አድናቂዎቹ በላቲንኛ ቋንቋ “No Lo Vames a olvidar!” ማለትም “ሕዝባዊውን ጀግና ምንጊዜም አንረሳውም፣ ሕልሙን እውን ለማድረግ ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ሲሉ የገዳዮቹን ወሽመጥ የሚቆርጥ መፈክራቸውን በሕብረት ድምጽ አስተጋብቷል።  

(፮ቱ ፋና - ወጊዎች - በፀሐዬ አለማ) 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
117 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us