የዳዊት መቀባት

Wednesday, 19 July 2017 13:16

 

አምላክ ውስጥን እንጂከ፣ መች አየ ቁመና

ታናሽ ብላቴና

ልቡ ተመዝና

በቀንደ ሳሙኤል፣ በዘይት ሹመት ጸና።

የእግዚአብሔር ጣቶቹ፣ ሁሌ ሚሸክፉ

ከፍ ብሎ እንዲበር፣ ተበጀለት ክንፉ።

ዳዊትም መጠቀ፣ ወደ ላቀ ማዕረግ

ፈጣሪ ሲፈልግ

እንኳን እረኛና፣ በጎች የሚያግድ

ለክብር ያበቃዋል፣ ያነሰውን ከግርድ።

(“የሚበርድ ፀሐይ”፤ ከተሰኘው የግጥም መድብል ኤርምያስ ሚካኤል (ሕርይቲ))

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
171 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us