ማተሚያ ቤት ለማስፋፋት የተደረገ ዐቢይ ክንውን

Wednesday, 19 July 2017 13:16

 

·         ልዑል አልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ መስከረም 14 ቀን 1914 ዓ.ም በግቢያቸው ውስጥ አንድ ማተሚያ ቤት አቋቁመው መፃሕፍትን ማሳተም ጀመሩ። በአለቃ ገብረ መድህን የሥራ ክፍል “በሥራ ላይ ከነበሩት ቁም ፀሐፊዎች አብዛኛዎቹ ወደ ማተሚያ ቤት ተዛውረው እንዲሠሩ ተደረገ።

·         በዚህ ማተሚያ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የታተሙት መፃሕፍት ዮሐንስ አፈወርቅና ማር ይስሐቅ ሲሆኑ ከዚያም ቀጥሎ አርባዕቱ ወንጌልና ምሳሌያተ ሰሎሞን፣ እነዚህንም የመሳሰሉ ሁሉ እየታተሙ ወጥተዋል። ከደራሲያንም ወገን ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ድርሰታቸውን አሳትመውበታል።

·         ይሄ ማተሚያ ቤት መጀመሪያ ሲቆም ሥራ አስኪያጁ አንድ ኢጣልያዊ ነበር። ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን ገብረ ክርስቶስ ተክለ ሃይማኖት የተባለ የሐማሴን ሰው በስፍራው ተተክቶ ዲሬክተር ሆነና ሥራውን እያስፋፋ አሳደገው። ይህ ሰው በሥራው እጅግ ትጉህና ብርቱ ነበር እንደ ይነገራል።

·         የማተሚያ ቤቱ ስም በዚያ በመጀመሪያው ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ የልዑል ራስ ተፈሪ መኮንን ማተሚያ ቤት ተባለ።

·         ከሦስት ዓመት በኋላ በ1917 ዓ.ም ብርሃንና ሰላም የተባለ የሳምንት ጋዜጣ ተመሥርቶ የሚታተምበት ስለሆነ የማተሚያ ቤቱም ስም ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት እየተባለ ይጠራ ጀመር። እስከ 1967 ዓ.ም ደግሞ ብርሃንና ሰላም ቀ.ኃ.ሥ. ማተሚያ ቤት ይባል ነበር።

·         ብርሃንና ሰላም በኋለኛው ዘመን በተደረገለት መስፋፋት በኢትዮጵ ዘመናዊ የኅትመት ታሪክ ዝነኛ ማተሚያ ቤት በመሆን ሊዘልቅ ችሏል።

(“ኅብረ ኢትዮጵያ” ቅፅ ሁለት - ቴዎድሮስ በየነ)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
225 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 996 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us