በልተሻል አደራ

Wednesday, 26 July 2017 13:29

 

ወደድኩሽ ለማለት ምክንያት ባይኖረኝ

ለመጥራት አቅቶኝ አንዱም እንዳይቀረኝ

እንደው አልኩሽ እንጂ ፍቅርሽ መቼ ሆነኝ

      ተወዳጅ ቆሞ ቢያይ የወዳጁን ወስዶ

      ችሎ መቼ ያድራል ያ’ሳብ መንገድ ሂዶ

      ያላየ አያምንም ወይ ነዶ! ወይ ነዶ!

ነግ በኔ አትርሺ የሰው ልጅ ነሽና

የጭንቅ ቀን ስታልፍ እንዲያ እንዲያ ሁና

ቦታውን ቀየረው እጣችን ወጣና

ባ’ንዱ ቀብር ማግስት አንዱ ተነሳና

ትላንት ሽምግልና ይላል እንደገና (2x)

      ስጠራሽ አልሰማሽ ለፍቅር አዝመራ

      ቀርተሻል ለሰርጌ ልቤ ተሞሽራ

      ይግባኝ አትጠይቂ ዙፋንሽ ተሽራ

ዛሬ ለምን መጣሽ በልተሻል አደራ     

(ምንጭ- “ሞትን ሞት ይሙተው” - በፊይሶ ተመስገን)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
127 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us