እንደ ወርቅ ከእሣት ነጥራ የወጣችው ኮረዳ

Wednesday, 26 July 2017 13:31

 

ኦፕራ ዊንፍሬይ በራስ መተማመኗን ድልድይ አድርጋ ገና የ4ኛ ክፍል ተማሪ ህፃን ሳለች በአዕምሮዋ ውስጥ የቀረፀችው ትልቁ ምስሏን ከወዲሁ መጨበጥ ጀምራለች።

- በ1971 በት/ቤት ክለቦች ደረጃ በተዘጋጀ የንግግር ውድድር ከልጅነቷ ጀምራ ባዳበረችው ክህሎቷ አማካይነት በማሸነፍ የአራት ዓመት የኮሌጅ ትምህርት ስኮላርሺፕ ተሸላሚ ለመሆን በቃች፣

- በዚያው ዓመት በዋይት ሐውስ አዘጋጅነት በኮሎራዶ በተካሄደው የወጣቶች ኮንፍረንስ ላይ ከአባቷ ጋር ትኖርባት የነበረችውን የናሽቪል ከተማ የምትገኝበት የቴኒሲ ግዛትን በመወከል ተካፍላ ስታበቃ ወደ ናሽቪል እንደተመለሰች WVOL የተሰኘ አካባቢያዊ ሬዲዮ ጣቢያ ቃለ መጠይቅ አደረገላት፣

- በ17 ዓመቷ የናሽቪሊው WVOL ሬዲዮ ጣቢያን በመወከል የእሣት አደጋን የመከላከል ግንዛቤ ለመፍጠር በተዘጋጀድድር ላይ እንድትሳተፍ ሬዲዮ ጣቢያው ያቀረበላትን ጥያቄ ያለማቅማማት በልበ ሙሉነት በመቀበል ተወዳድራ በአንደኝነት ደረጃ አሸነፈች። በዚህ አጋጣሚ ነበር የሬዲዮ ጣቢያው የንግግር ልዩ ተሰጥኦዋንና ክህሎቷን ከግምት ውስጥ በማስገባት በትርፍ ሰዓት የዜና አንባቢነት የቀጠራትና የጋዜጠኝነት ሙያዋን ያሟሸችበት የመጀመሪያ እድሏን ከፈተላት፣

- እዚያው ናሽቪል ከሚገኘው የሲ.ቢ.ኤስ. አካባቢያዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ በምሸት ዜና አቅራቢነት እንድትሰራ የተሰጣትን እድል በፀጋ በመቀበል የዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን ከሁለቱ የብዙኃን መገናኛዎች ስራ ጋር አጣጥማ ማስኬዷን ተያያዘችው። በዚህም በናሽቪል በእድሜ ከሁሉም ያነሰችና የመጀመሪያዋ አፍሮ-አሜሪካዊ ጋዜጠኛ ለመሆን በቃች (ይህ የአፍሮ አሜሪካዊቷ ታላቅ ስኬት እየተመዘገበ ያለው የጥቁሮችን ነፃነት ታጋዩ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኔር በተገደለ አስር ዓመት እንኳን በማይሞላ ጊዜ ውስጥ መሆኑን ልብ ይሏል) (ከገፅ 53-54)

                    (ምንጭ- “ከ፮ቱ ፋና - ወጊዎች” መጽሐፍ የተወሰደ /በፀሐዬ አለማ/)¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
168 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 178 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us