የክብረ ንፅሕና ጋራዥ

Wednesday, 09 August 2017 12:44

 

ሕይወትን የሚፈጥንም ሆነ የሚቀጥፍ፣ የዓለምን ሕዝብ የሚያስገርምም ሆነ የሚያስረግም አዲስ ነገር ሲተዋወቅ ጥሞናን ይሰርቃል። በተለይ ክስተቱ የሆነው/ እየሆነ ያለው እዚሁ አጠገብህ ከሆነ ምን የደስታ ስካር ውስጥ እየዋኘህ ቢሆን ሽራፊ ትኩረት ለመስጥ አትሰስትም። የዘመን ሂደትም የነገሮችን ዜና የሚሆን የማስደነቅና የማነጋገር ርዕስነት ደረጃ ያወርደዋል። ዛሬ ላይ ለአንድ የአገሬ ሰው አሜሪካ ውስጥ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ቢደረግ፣ መንኮራኩር ቢመጥቅ፣ ከውሃ በታች ሕንጻ ቢገነባ በመገረም “ያልሰማህ ስማ” ሲል ዜናውን በመበተን ጉንጩን አያለፋም። የተጠቀሱት ድርጊቶች ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈፀሙ ቢሆን ኖሮ ሁላችንም ላይ የአፍዝ አደንግዝ ቫይረስ ይለቁብናል። ፈረንሳይ ውስጥ ስላለ የድንግልና ጥገና መስማት ያስገርማል። ክስተቱ “ኢትዮጵያዊ ሲሆን ግን ከማስገረም በላይ ስሜቱ ከፍ ሊል ይችላል።

“የኛ ሰው ገመና” በተሰኘው መጽሐፌ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ እንደ አንዳንድ የውጪ አገራት ሁሉ ድንግልና እየተሸጠ መሆኑን አሳይቻለሁ። ከርዕሱ ብዙም ፈቀቅ ሳልል “ላለፈ ክረምት ቤት እንደሚሠራ” የሚጠቁም ግልጽ ያልወጣ እውነታን እንካችሁ ልል ነው። “ጉዳዩ፡- ድንግልናን ስለማሳደስ ይመለከታል።”

ሸገር ድንግል መሬቷን ሸጣ ስታገባድድ ድንግል ሴቶችን ለገበያ ማቅረብ መጀመሯን አውርተን ሳንጨርስ “ድንግልናን ማደስ” መጀመሯን ርዕስ ልናደርግ ነው፤ አዲስ አበባ ለመኪኖቿ ሳይሆን ለሴቶቿም ክብረ ንፅሕና ጠጋኝ “ጋራዥ አለኝ” እያለች መሆኗን ልናወራ። ክብረ ንጽሕና ቢገሠሥ ክብረ ንፅሕና ይመለሳል!

                          (“የዘመኑ ሴራ” - ከአቤል ዓለማየሁ)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
150 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1092 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us