የአንድ ወንዝ ፈተና

Wednesday, 16 August 2017 12:28

 

ገበሬና ካህን ከአንድ ኢንጅነር ጋራ፣

ይሄዱ ነበረ እጅግ ሩቅ ስፍራ፤

እየተጫወቱ የሰማይ - የምድሩን፣

በሰፊ እያወጉ ታርክ፣ ኑሯቸውን፣

ሲወጡ - ሲወርዱ ዳገት፣ ቁልቁለቱን፤

ባልጨረሱት መንገድ - ባልፈፀሙት ጉዞ፣

ወንዝ ገጠማቸው ያውም ጎርፍ አርግዞ፤

አራዊት በበዛው እንዲህ በሚያስፈራ፣

ማደር ያስቸግራል መቼም በዚያ ስፋራ፤

የውሃውን ሙላት ጎርፉን በደንብ አይቶ፣

      ፀሎት መፅሀፉን ከጉያው አውጥቶ፣

      አይኑን ጨፈነና እጆቹን ዘርግቶ፣

      “እንደሙሴ ከፍለን እንድናልፍ ውሃውን . . .፣”

አላቸው ካህኑ “በሉ እንፀልይ አሁን!”፤

“ቀይ ባህር በበትር ተከፍሏል፤” እያለ፣

“ኢያሪኮ ፈርሷል፤ ይወድቃል!!” እያለ፣

ካህኑ ለፀሎት በእምነት በርከክ አለ፤

ያ ቁስ አካላዊ የታወቀ ኢንጅነር፣

የዚያ ካህን ሀሳብ አልጣመውም ነበር፤

በትልቅ ወረቀት ፕላን እያነሳ-እየዘረዘረ፣

ድልድይ እንዲሰራ ሀሳብ ሰነዘረ፤

“ድልድዩ ይጀመር!!” አለ ኢንጅነር ቀርቦ፣

በእርሳስ የነደፈው ፕላኑን አንብቦ፤

የሁለቱን መላ ገበሬው ግን ሽሮ፣

“ምኖቹ ገጠሙኝ?” እያለ ተማርሮ፤

መፍትሄ ያለውን እሱም ያሄን ብሏል፣

“ውሃው እስኪጎድል መጠበቅ ይሻላል።”

/ምንጭ- “የተገለጡ ዓይኖች” የግጥም መድብል ከሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል)/¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
120 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 926 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us