የጥጃ ምስል

Wednesday, 23 August 2017 12:18

 

አወይ ላምዋ

ተ ላ ላ ዋ

አርግዛ እሳት - አምጣ እሳት

ወልዳ በዱር - እዛፉ ስር

ጅማት ነገር ውትርትር

ቢሞትባት ስትጠግበው ቆዳውን ገፈው አውጥተው

ሥጋውን በገለባ ሰግተው አጥንቱን በእንጨት አጥንተው

ቃ ም ቆ - ተ ጠ ር ን ቆ

ምስለ ጥጃ ሕይወት አልባ

አፅመ እንጨት ወገለባ

ከጡትዋ ስር ተሸጉጦ

ላያስወርድ ልጎ ንጦ

አወይ ላምዋ ተላላዋ

አለ መስሏት እምቦሳዋ

ከሞት ማዶም ፍቅር ቻሪ ለሙት ቁበት።

ከወተትዋ ዥንቅ ዥንቅ

አላቢዋም ፍንድቅ ፍንድቅ

ሲያታልላት ቂቁይ ዋሾ

በኩርማኑ ጨው መላሾ

አይ ላምነት የዋህነት አናትነት

ፍቅረ እናት እስከ ሲኦል እስከ ገነት።

ቁረንጮ ላሽ ላምነት ላሽ

ቆዳ ነካሽ።

ሳታውቅ እውነት

ነክሳ ቁርበት

ከረመች ስትታለል ስትታለብ

እንደታወርድ ለወተትዋ ስትቀለብ

ግን እኮ ብትሰረስረው

ከደረቀው ጅራቱ ስር ብትፈታታው

ትበላ ነበር ከጭዱ

ከሥጋው ከገለባው ከጉዱ።

                  የወንድ ምጥ - ከይስማዕከ ወርቁ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
85 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us