ከአድዋ ጦርነት በፊት አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ መሳፍንትና መኳንንትና ባለ ሰዓት እንደ ነበሩ የሚያሳይ አንድ ገጠመኝ

Wednesday, 23 August 2017 12:21

 

በአድዋ ጦርነት ለመሳተፍ ሊቀ መኳስ (በኋላ ራስ) አባተ ቧያለው ሰራዊታቸውን አስከትተው ወደ ግንባሩ ያመራሉ። አብረዋቸው ከነበሩት አንዱ የዚያን ጊዜ ልጅ (በኋላ መልአከ ፀሐይ) አፈወርቅ ናቸው።

ለአድዋ ዘማች ሀገረ ገዢዎች በግዛታቸው ለሚያልፈው መስተንግዶ እንዲያደርጉ ታዞ ነበርና ከአንድ ሀገረ ገዢ ቤት ሲደርሱ ድንኳን ተጥሎ ፍሪዳው ታርዶ እንጀራው ቆሎው በገበታ ላይ ተሰጥቶ ጠላው ጠጁ በጋን ተሹሞ ሲጠባበቅ አገኙት። ሊቀ መኳስ አባተ እንደ አጋጣሚ እዚያ የደረሱት ዓርብ የፆም ቀን ነበር። ጊዜውም ገና ረፋዱ ላይ ነበር። እርሳቸውም አሁን ሰዓቱ ገና ሶስት ሰዓት ነው፤ እንዴት በጠዋት እንሰፍራለን ጓዝ እንዳይሰፍር ንገሩ መንገዳችንን እንቀጥላለን አሉ። ሰራዊቱ ግን ከቤቱ ከወጣ ስምንት ቀን አልፏልና ቂጣውም ደርቆ ጉዳት ላይ ነበርና እኩሉ ማንም ሳያዘው ከብት አቁሞ ሲፈታ እኩሉ ሲያመንታ መልአከ ጸሐይ አፈ ወርቅ አይተው በጣም ሃዘን ስለገባቸው ወደ ሊቀ መኳስ አባተ ዞር ብለው ለመሆኑ የእርስዎ ሰዓት ስንት ይላል? ቢሏቸው ሦስት ሰዓት አሉ። የራሳቸውንም የእጅ ሰዓት ተመለከቱና የኔም ሶስት ሰዓት ይላል፤ ስለዚህ ስድስት ሰዓት ማለት ነው አሉ። ደግመው አጠገባቸው ከነበሩት አንድ መኮንን ዞር ብለው የእርስዎስ ስንት ይላል? ብለው ጠየቋቸው። የተጠየቁትም ሰው ሰዓታቸውን ተመልክተው ሶስት ሰዓት አሉ። እንግዲህ ዘጠኝ ሰዓት ማለት ነው። የታዘዘውስ ይህ አይደለም? ብለው አገበታው ላይ ከነበረው ንፍሮ ዘገን አድርገው ቃም ቃም ሲያድጉ ሊቀ መኳስ አባተም መኳንንቱም እንደዚህ አደረጉና ከዚያ በኋላ አዳር እዚያው እንደሚሆን ተለፈፈ። በማግስቱም የታረደው ሥጋ ሲበላ አርፍዶ መንገዳቸውን ቀጠሉ።

                              ኅብረ ኢትዮጵያ - ቴዎድሮስ በየነ 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
103 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 914 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us