ሌባ ለአመሉ. . .

Wednesday, 30 August 2017 12:54

 

ሰሞኑን ከሊውሲያና ከተማ ፖሊስ የለቀቀው የካሚራ ቅጂ አለምን ወቸ ጉድ! አሰኝቷል። ነገሩ እንዲህ ነው። የ37 ዓመቷ ወይዘሮ ሴኮኒ ጅንስ ወደ አንድ የመጠጥ መደብር ያመራሉ። እናም በመደብሩ ውስጥ ያደረጉትን አድርገው ወደ መደብሩ ገንዘብ ተቀባይ በመሄድ የአንድ ጠርሙስ መጠጥ ዋጋ በመክፈል ላይ ሳሉ በካሜራ ይከታተሏቸው የነበሩ የመደብሩ የፀጥታ ኃይሎች ሴትየዋን ለፍታሻ ይወስዷቸዋል። በተደረገው ፍተሻም ወይዘሮ ጆንስ 18 ጠርሙስ የወይን ጠጅ እና ሌሎች መጠጦችን ደብቀው ተገኝተዋል። የሚገርመው ደግሞ ሴትየዋ ጠርሙሶቹን የደበቁበት ሁኔታ ነበር። ሰፋ ደልደል ያለውን የሰውነት ቅርፃቸውን በመጠቀም አብዛኞቹን ጠርሙሶች በጡት ማስያዛቸው እና በውስጥ ሱሪያቸው ውስጥ የደበቁ ሲሆን የተወሰኑትን ደግሞ በቦርሳቸው ውስጥ ደብቀው ተይዘዋል።

ፖሊስ ሴትየዋን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ከመደብሩ ውስጥ ጠርሙሶቹን ሲደብቁ የሚያሳየውን ቪዲዮም አለም ይመልከተው ሲል በዩቲዩቭ ለቆታል ሲል ያስነበበው ዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርናሽናል ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
51 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us