ከምሁራን አንደበት

Wednesday, 30 August 2017 12:55

 

-    ጠቢብ ሰዎች የሚያወሩት የሚናገሩት ነገር ስላላቸው ሲሆን፤ ሞኝ ሰዎች ግን የሆነ ነገር መናገር ስላለባቸው ብቻ ነው የሚያወሩት። (ፕላቶ)

-    ሞኝ ሰው ከጠቢብ ሰው መልስ ከሚማረው ይልቅ ጠቢብ ሰው ከሞኝ ጥያቄ የሚማረው ይበልጣል። (ብሩስ ሊ)

-    ህይወት ለጠቢብ ሰው ህልም፣ ለሞኝ ጨዋታ፣ ለሀብታም ቀልድ ለደሃ ደግሞ አሳዛኝ ናት (ሾሎም አሊቸም)

-    የህይወት አሳዛኙ ነገር ለማደግ ፈጣን መሆናችን እና ጠቢብ ለመሆን መዘግየታችን ነው። (ቤንጃሚን ፍራንክ ሊን)

-    የጠቢብነት ዓላማው ምቾትን ማግኘት ሳይሆን ህመምን ማስወገድ ነው። (አርስቶትል)

-    ጅል ይቅርታም አያደርግም ነገርም አይረሳም፤ የዋህ ይቅርም ይላል ነገርም ይረሳል። ጠቢብ ግን ይቅር ይላል ግን አይነሳም። (ቶማስ ዛስ)

-    ሁልጊዜም ወደፊት መመልከት ጠቢብነት ነው። ማየት ከሚቻለው በላይ አርቆ መመልከት ግን ከባድ ነው። (ዊንስተን ቸርችል)

-    ሞኝ በስተመጨረሻ የሚያደርገውን ነገር ጠቢብ በመጀመሪያው ሙከራ ያደርገዋል። (ኒብሎ ማቺቬሊ)

-    መቅሰፍት የሚመጣብን ሊያሳዝነን እና ሊያስጨንቀን ሳይሆን ጠቢብ ሊያደርገን ነው። (ኤች ጂ ዌልስ)

-    ብልጥ ሰው ይሳሳትና ከዚያ ከስህተቱ ይማራል። ያን ስህተትም አይደግመውም። ጠቢብ ሰው ግን ብልጥ ሰው ፈልጎ ስህተቶችን እንዴት ማስወገድ እንዳለበት ይማራል። (ሮይ ኤች ዊሊያምስ)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
157 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us