ቢራ አንሸራሻሪው

Wednesday, 06 September 2017 14:00

 

ጀርመን በዓለማችን ላይ ቢራ አምራች ከሆኑ ሀገሪት አንዷ ናት። ሰሞኑን በሀገሪቱ በተካሄደ አንድ ፌስቲቫልም ጀርመናዊያን ቢራ ጠማቂዎች ብቻም ሳይሆኑ ቢራ ነክ በሆኑ ነገሮች የተካኑ መሆናቸውን የማያሳይ ነገር ተሰምቷል። ሮይተርስ እንዘገበው አንድ ጀርመናዊ በፌስቲቫሉ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የቢራ ብርጭቆዎችን ተሸክሞ በመጓዝ የዓለም ክብረ ወሰንን መበጠስ ችሏል።

 

ኦሊቨር ስትራምፕፌል የተባለው ጀርመናዊ 29 የቢራ ብርጭቆ (በተለምዶ ጃምቦ የሚባሉትን) በሁለት ትሪዎች ላይ ደርድሮ 40 ሜትሮችን በመጓዝ ነው ስሙን በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ማስመዝገብ የቻለው። እነዚህን ሜትሮች ከተጓዘ በኋላም ብርጭቆዎቹን ሳያወርድ ያለ ምንም መንገዳገድ መቀመጥ ችሏል። ኦሊቨር ውድድሩን የጀመረው 27 ብርጭቆዎችን በመሸከም የነበረ ሲሆን፤ ቀስ በቀስ ቁጥሩን እየጨመረ በመምጣት ለዚህ ደረጃ መብቃቱ ተገልጿል። በመጨረሻም 31 ብርጭቆዎችን ተሸክሞ በመጓዝ ቁጭ በማለት ክብረወሰኑን ለማድረግ ሞክሯል። ይህ ከብረ ወሰን በ2014 በታደር ውድድር 25 ብርጭቆዎችን 69 ኪሎግራም ክብደት) ተሸክሞ በመጓዝ ተይዞ የነበረ ሲሆን አሊቨር በ4 ብርጭቆዎች በማሻሻሉ ለዚህ መብቃቱ ተገልጿል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
160 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1095 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us