ብቸኝነት ማለት

Wednesday, 06 September 2017 13:55

 

ከሰዎች መነጠል. . .ለብቻ

መቀመጥ. . . አይደለም ትርጉሙ

ጓደኛ አለመኖር ብቻ ቀን

ማሳለፍ እሱ አይደል ህመሙ

      ብቸኝነት ማለት

ከሰው መንጋ ውሎ. . . ከሰው ተቀላቅሎ

ባዶነት መሰማት

የናፈቁትን ድምጽ ከሩቅ እየሰሙ በውስጥ ማዋራት

የናፈቁትን መልክ . . .ለብቻ

እያለሙ በናፍቆት መብከንከን

ቅርብ የሌለን ጠረን በፍንጫ

እየማጉ. . . በሽታው መታጠን

የድሮን ትዝታ ዛሬ እያሰቡ. . .፤

ከሃሳብ ማህደር ደግመው ያነበቡ.  . .

በናፈቁት ሰው ድምጽ የቅርቡን ሲጠሉ

የሚልቅን ጠረን. . . ካጠገብ አስቀምጠው

በሩቅ ሰው ሩሩሩሩቅ ጠረን. . . ባሳብ ሲነጠሉ

      ድሮ የሳቁትን ደግመው እያሰቡ

      ሀዘን መሃል ሆነው ለብቻ ሲፈልጉ

      ድሮ ያዘኑበትን ዛሬ እያስታወሱ

      ከሞቀ ሳቅ መሃል ለብቻ መንሰቅሰቅ ማልቀስ ሲፈልጉ

ብቸኝነት ማለት . . . ትዝታ ማለት ነው።

ማለት ነው ትዝታ

ከብዙ ሰው መሃል ብቻነት መስማት

ቀን የውሸት ስቀው ብቻ ማልቀስ ማታ

      ልክ እንዳሁናችን ካጠገቤ ’ያለህ እንደምትናፍቀኝ

      ፍቅራችን አርጅቶ ምልክት በቀረው በትዝታ ሽበት ዛሬ እንደምትታየኝ

      ብቸኝነት ማለት የትዝታ ድርሳን ነው የናፍቆት ክርታስ

      ውዴ ፍቅሬ እያሉ በቋጠሩት ትላንት ዛሬን አንጀት ማራስ

      “እይዋት ስትናፍቀኝ ካጠገቤ እያለች” የሚል ዘፈን ማቆም በመሃመድ ዘፈን ምንድነው ትዝታ ብቻ ከትካዜ መስጠም።

                  ሄለን በድሉ (ከፌስ ቡክ)  

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
453 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us