እውነትም መምህር!

Wednesday, 13 September 2017 12:29

 

የቴክሳሱ ፕሮፌሰር ለአንዲት ተማሪያቸው ያደረጉት ነገር በበጐ አርአያነት ከመጠቀሱም በላይ የዓለም መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል። በቴክሳስ ኤ ኤንድ ኤም ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ሄነሪ ሙሰማ ትምህርት በሚሰጥበት ዩኒቨርሲቲ አንዲት ተማሪያቸው ልጇን የሚይዝላት በማጣቷ ምክንያት ትምህርት እንዳያመልጣት አግዟል ተብሏል። ኢሜት የተባለችው ተማሪ ልጇን ወደ ትምህርት ቤት ይዛ ብትመጣ ትምህርት ለመከታተል ልጇን የምታስቀምጥበት የህፃን መቀመጫ እንደሌለ ትረዳለች። በመሆኑም ለመምህሯ ይሄንን ችግሯን በመግለፅ ወደ ዩኒቨርሲቲው ልትመጣ አለመቻሏን በኢሜል መልዕክት ትልክለታለች። መምህሩም ለተማሪው የላከላት መልዕክት ከጠበቀችው በጣም የተለየ ሆኖ ነበር ያገኘችው። “እባክሽ ልጅሽን ወደ ዩኒቨርሲቲው ይዘሽው ነይ” ብሏታል።

 

ልጇን ለብቻዋ የምታሳድገዋ ወጣት እናትም በተባለችው መሠረት ልጇን ይዛ ወደ ዩኒቨርሲቲ መጥታለች። በመቀጠልም ያደረገው ነገር የባሰ ሰዎችን አስገርሟል። ተማሪዋ ቁጭ ብላ ትምህርቷን ስትከታተል መምህሯ ግን ልጁን በአንድ ክንዱ ታቅፎ ክፍል ውስጥ እየተንጐራደደ ለተማሪዎቹ ትምህርት ሲሰጥ የሚያሳየው ቪዲዮ ተማሪዋ ከለቀቀች በኋላ በርካቶች ስለመምህሯ ያላቸውን አስተያየት እየገለፁ ይገኛሉ። አሜት የተባለችው የፕሮፌሰሩ ተማሪም “ለኔ ከዚህ የበለጠ የተለየ ነገር የለም። እናት በመሆኔ ከምንጊዜውም በላይ የተደሰትኩበት ጊዜ አሁን ነው።” ስትል ገልፃለች። “ፕሮፌሰሩ ችግሩን ለመፍታት የወሰዱት እርምጃ ለዓለም ሊገለፅ ይገባዋል” ያለው ዘገባው ኢሜትም በዚህች ችግር ሳቢያ ከመመረቅ ልትስተጓጐል የነበረ ሲሆን፤ መምህሯ ባደረገላት እገዛ ብቻ ትምህርቷን አጠናቃ ልትመረቅ ችላለች ተብሏል።

ዘገባው የዴይሊ ሜል ነው።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
187 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 963 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us