ውርስ

Wednesday, 20 September 2017 14:04

ውርስ

የባለድል ወገን

      ሐውልቱ ስር ቆሞ፤

በግርምት ፈዞ

      በሃሳብ ቆዝሞ።

ድንጋዩን አንብቦ

      ጥበብ እየቀዳ፤

መንገዱን ለይቶ

      ለድል ተሰናዳ።

***

ደ’ሞ ተሸናፊ

      ሐውልቱን እያየ፤

ህመሙ አገረሸ

ውስጡ ተሰቃየ።

ቁስሉ አመረቀዘ

      ስሜቱ ጠጠረ፤

በሐዘን ተቆራምዶ

      ልቡ ቂም ቋጠረ።

ድንጋዩን አናግሮ

      ጥላቻ ሰነቀ፤

ወኔውን አፅንቶ

ለበቀል ታጠቀ።

***

      ታዲያ ምን ይገርማል

            ልጆች ባይስማሙ?

      ላላለቀ ውጊያ

            ሐውልት ‘ሚያቆሙ፤

      አዳራሽ ‘ሚያንፁ

            መንገድ ‘ሚሰይሙ።

      ልዩነት አድማቂ

            አባቶች እያሉ፤

      ለምን ይገርመናል

            ልጆቹ ቢጣሉ?

/ምንጭ- ንፋስ ያነሳው ጥላ (የግጥም መድብል) - በብርሃነሥላሴ ከበደ (ያ’ዲስ ልጅ)/¾

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
158 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 932 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us