የዓለማችን አስጠሊታ ውሻ

Wednesday, 20 September 2017 14:08

Oneoneከሰሞኑ በተደረገ አንድ ፉክክር የዓለማችን እጅግ አስጠሊታዋ ውሻ ታውቃለች። ለ29ኛ ጊዜ በተደረገው የዓለም የመስጠሎ ውሾች ውድድር ላይ ከ13 አስጠሊታ ውሾች ጋር ለፉክክር የቀረበችው ማርታ የተባለች ውሻ በማሸነፍ ሽልማቷን ወስዳለች ተብሏል። የ3 ዓመት እድሜ ያላት እና 125 ፓውንድ የምትመዝነዋ ማርታ በካሊፎርኒያ በተደረገው ውድድር ላይ የመስጠሎዎች መስጠሎ ውሻ ተብላ ነው የ1ሺህ 500 ዶላር ሽልማቷን ተቀብላ የአሸናፊነት አክሊሏንም የደፋችው። ማርታ እጅግ አስጠሊታ ከመሆኗም በላይ ግዙፍና ለመሸከም አስቸጋሪ የሆነ ክብደት ያላት ውሻ ናት። ለውድድሩ ከቀረቡ ውሾች መካከል አሳዳጊዋ ልትሸከማት ያልቻለች ብቸኛዋ ውሻም ነበረች። በመሆኑም ማርታ ማንም ሳይሸከማት አስፈሪ ፊቷን ይዛ በመድረክ ላይ ስትጐማለል በተመልካቾች ዘንድ እጅግ አስፈሪ ስሜትን ፈጥራ እንደነበር ተገልጿል።

 

ውሾቹ አስጠሊታ ተብለው ለመመረጥ የተቀመጡላቸው መስፈርቶች ያሉ ሲሆን፤ ዋና ዋናዎቹም በተመልካቾች ላይ እጅግ የሚያስጠላ ስሜትን መፍጠር፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያዩዋቸው ማስፈራት እና ማስጠላት እንዲሁም በመድረክ ላይ ያልተለመደ ነገርን ማድረግ ይጠቀሳሉ። በመሆኑም ማርታ አነዚህን ነገሮች ሁሉ አሟልታ በመገኘቷ የ2017ቷ የዓለማችን አስጠሊታ ውሻ ተብላ ተመርጣለች። ከማርታ ቀጥላ የ16 ዓመት እድሜ ያላት ከብራስልስ የመጣችዋ ሞኤ የተባች ውሻ አስጠሊታዋ የዓለማችን ውሻ ተብላለች ሲል የዘገበው አሶሼዬትድ ፕሬስ ነው።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
151 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 862 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us