መቼ ነው?

Thursday, 28 September 2017 14:31

 

መቼ ነው?. . . ተዋደው

ተፋቅረው . . . ተቃቅፈው

እጅ ለእጅ . . . ሆነው

ተጣምረው . . . ተባብረው

ተቃርበው . . . ተያይተው

በአንድ ገጽ . . . ስቀው

ከአንድ ማእድ . . . ቆርሰው

ስለ ቅን . . . ተቀኝተው

ስለ ቅን . . . ዘምረው

አንተ . . . ትብስ

አንተ . . . ትብስ

ብለው . . . ተባብለው

መክረው . . . ተመካክረው

ደምቀው . . . ተደማምቀው

      መቼ ነው?

            ኧረ!

            ኧረ!

            ኧረ!

      መቼ ነው?

እውነትና ፍቅር

ከአንድ ምንጭ ፈልቀው

በአንድ መቅረዝ በርተው

ለብርሃን . . . ፈክተው

ለብርሃን . . . ስቀው

ስለብርሃን . . . ብለው

ብርሃን . . . ለመስጠት

በብርሃን . . . ሚምሉት?

መቼ . . . ነው?

      ኧረ!

      ኧረ!

      ኧረ!

መቼ . . . ነው?

/ምንጭ- ተኚ ያጣሌሊት እና ሌሎችም ግጥሞች - በሠራዊት ዮሐንስ/

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
102 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us