የማርቲን ሉተር ኪንግ ምርጥ አባባሎች

Thursday, 28 September 2017 14:33

 

-    በህፃንነቴ ባሪያ አልነበርኩም፣ ሆኖም ነፃ መሆኔንም አላውቅም ነበር።

-    በጉርምስናዬ ስለነፃነት አብልጬ የምሞት ነበርኩ፣ ሆኖም ስለነፃነት የነበረኝ ግንዛቤ የጠራና የጠበቀ አልነበረም።

-    በአሮጌ ወጣትና በጅምር ጐልማሳ ድንበር ላለው የህሊና ነፃነቴ አጥብቄ እሻታለሁ ብቻ ሳይሆን እጅግ አድርጌ አከብራታለሁ።

-    በህይወቴ የቀመስኳቸው መራራ ሐሞቶች ለነፃነቴ የተከፈሉ የመስዋዕትነት ዋጋዎች ናቸው።

-    ተፈጥሯዊ ነፃነቴን ጠልቄ እመረምራታለሁ ብቻ ሳይሆን በእውነት እገነዘባታለሁ። ሳውቃት እታገላለሁ ብቻ ሳይሆን ልኖራት እደክማለሁ።

-    ድካሜ ውስጥ ጣፋጭ ስቃይ አለ

-    የማልፈራው፤ በደግነትና በእውነተኛነት መካከል የተመላለስኩ እንደሆነ ነው።

-    ከጌታዬ ሦስት ነገሮችን አጥብቄ እፈልጋለሁ። አንድ ጥበብ፣ ሁለት ጥንካሬ፣ ሦስት ፍቅር። ከእነዚህ ከሦስቱ የበለጠ የምሻው ግን ፍቅርን      ነው። ፍቅር ሲኖረኝ ሁሉም ጥሩ ነገር አለኝ።

-    ነፃ የምንሆነው ስለነፃነት ባለን ግንዛቤ ልክ ነው።

-    ነፃ የምሆነው ሳልፈራ ስቀር ብቻ ነው።

(ምንጭ:- ንጥር)¾

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
258 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us