መጋቢት ሚያዚያ ግንቦት

Thursday, 28 September 2017 14:34

 

ኤስ.

ወዳጄ በዲያብሎስ ሴራ መከበባችንን ላንተ ማብራራት የለብኝም። ያማ ባይሆን ኖሮ ቤተመንግስቱ ለተጨማሪ ሺህ ዓመታት ፀንቶ ይቆይ ነበር። ምክንያቱም የትኛውም ቤተመንግስት በፈቃዱ አይወድቅም። ትናንት ወደ ገደል እየተንሸራተትን እንደነበር አላውቅም። በፈዘዘ፣ በታወረና በሲኦላዊ የመታፈን ሁኔታ ውስጥ፣ በራሳችን ከልክ በላይ በመተማመን፣ ራሳችንን በማወደስ ውስጥ ሆነን ወደ ፊት ሊመጣ የሚችለውን አላሰብንም ነበር። በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን ጐዳናው ያለማቋረጥ በተቃውሞ ሰልፍ ይሞላ ነበር። ሁሉም ሰው ሰልፍ ይወጣል፤ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ ሙስሊሞች ሁሉም መብታቸውን ይጠይቃሉ፤ ይጮሃሉ፤ ስብሰባዎችን ያደራጃሉ፤ መንግስትንም ይረግማሉ። ኦጋዴን የሰፈረው ሦስተኛው ክፍለ ጦር ስለማመፁ ሪፖርት መጣ። አሁን ጦር ሠራዊታችን በሙሉ አለመረጋጋት ውስጥ ገብቷል። ሠራዊቱ በባለስልጣናቱ ላይ ተነሳ። ሥርዓት አልበኝነቱና አሉባልታው ትዕግስትን እየተፈታተነ ባለበት ሰዓት ቤተመንግስቱ ውስጥም ሹክሹክታ ተጀመረ። መኳንንቱ ርስበርሳቸው በጥንቃቄ ነበር የሚተያዩት። ምን ይፈጠራል? ምንስ ይሰራል? ግቢው ተሰነጣጠቀ፤ ተሰባበረ፤ በጉርምርምታ ተሞላ። እዚህም እዚያም ቹ… ቹ… ቹ… ያለ ስራ ላይ ታች ስሉ፣ ሳሎን ሲሰባሰቡ፣ በምስጢር ሲያሴሩ መመቀኛኘቱና በቤተመንግስቱና በጐዳናው መሃል የነበረው ጥላቻና ፀብ እየበረታ፣ ሁሉንም ነገር እየመረዘ ነው።

 

 

ቀስ በቀስ ቤተመንግስቱ ውስጥ ሦስት አንጃዎች ብቅ ብቅ ብለዋል ባይ ነኝ። የመጀመሪያውና የአሳሪዎቹ አንጃ የስርዓትን መከበር በጽኑ የሚጠይቀው፣ ስርዓት አልበኞችን በማሰር፣ በመደብደብና በስቅላት በመግደል ላይ የሚያተኩረው አደገኛውና ግትሩ አንጃ ነው። ይሄ አንጃ በ65 ዓመቷ ወይዘሮ በንጉሰነገስቱ ልጅ በልዕልት ተናኜ ወርቅ ይመራል። ልዕልቲቱ ግትርና ጃንሆይን ስለደግነታቸው የሚተቹ ነበሩ። ሁለተኛው አንጃ የሊበራሎችን ቡድን ደካማና ፈላስፎች የሆኑትን ሰዎች ያካተተ ነበር። እነኚህ አማፂዎቹን ጠርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ እነሱ እንዲናገሩና የሚናገሩትም እንዲሰማ ሥርዓተ መንግስቱም እንዲሻሻል የሚያስቡ ወገኖች ነበሩ። እዚህ ትልቁ ድምፅ የአስተዋዩ፣ በመቻቻል የሚያምኑት ወደ ሰለጠኑ አገራት በተደጋጋሚ የተጋዙት የራስ ሚካኤል እምሩ ድምፅ ነው። ሦስተኛው የተንሳፋፊዎቹ አንጃ ሲሆን፤ ቤተመንግስት ውስጥ ብዙ አባላት አሉት። እነኚህ ፈፅሞ አያስቡም፤ ልክ ውሃ ላይ እንደሚንሳፈፍ ቆርኪ ባጋጣሚ ማዕበል ተነስቶ ወደ ወደቡ እንደሚያደርሳቸው ተስፋ ያርጋሉ። እናም ጊቢው ራሱን ወደ አሳሪዎች፣ ወገኞችና ተንሳፋፊዎች ሲከፋፍል እያንዳንዱ ወገን መከራከሪያዎቹን ማሰማት ጀመረ። በምስጢር፣ በድብቅ። ምክንያቱም ግርማዊነታቸው አንጃዎችን አይወዱም። እንዲሁም ወሬ፣ ጫና መፍጠርና ማንኛውንም አይነት ሰላም አደፍራሽ ነገር ይጠላሉ። ግና በአንጃዎቹ መኖር ምክንያት በተጀመረው መሰዳደብና መዳማት፣ መነካከስና መጋጨት፣ ጥርስ ነከሳውና ጥፍር ማሾሉ ቤተመንግስት ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ለቅፅበት ነፍስ ዘራ፤ ግቢው እንደገና ቤት ቤት መሽተት ጀመረ።

ምንጭ፡- ሚስጥራዊው ንጉሥ (ቀ.ኃ.ስ) - በዮሐናን ካሣ¾  

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
159 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1025 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us