ልጄን አላስከትብም ያለችው ሴት እስራት

Wednesday, 04 October 2017 12:52

 

ሰሞኑን የተሰማው ዜና በሰለጠነው ዓለምም ይሄ አለ እንዴ አስብሏል። በሚቺጋን ከተማ ነዋሪ የሆነችው እናት ልጄን ክትባት አላስከትብም በማለቷ ፍርድ ቤት ቀርባለች። ርብቃ ብሪደው የተባለቸው የሁለት ልጆች እናት የዘጠኝ ዓመት ወንድ ልጇ ክትባት እንዳያገኝ አድርጋች ሲል የኦክላንድ ፍርድ ቤት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷታል። ርብቃ እና የቀድሞ ባሏ ልጃቸውን በማስከተብ እና ባለማስከተብ ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻላቸው አባት ጉዳዩን ለፍርድ አቅርቦታል። ርብቃ ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ ልጇን ከማስከተብ ይልቅ ክትባቱን ማዘግየት በመፈለጓ ነበር ለፍርድ የቀረበችው። ፍርድ ቤቱም ልጇን በአንድ ሳምንት ውስጥ ማስከተብ እንዳለባት ካልሆነ ግን ላልተወሰነ ጊዜ በእስራት እንደምትቀጣ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። እርሷም “ልጄን ከማስከትብ ይልቅ የሚጠይቀውን ሁሉ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ” የማላምንበትን ነገር ከማደርግ ይልቅ የሚጣልብኝን ቅጣት ልቀበል ዝግጁ ነኝ ስትል ያላትን አቋም ለአክሽን ኒውስ ገልጻለች። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
131 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us