የዓለማችን ውድ ግብዣዎች

Wednesday, 04 October 2017 12:53

 

 

1.  የልኡል ዊሊያም እና ኬት ሰርግ

ይህ በልዑላዊያን ቤተሰቦች መካከል የተደረገ የሰርግ ስነ-ስርዓት በአለማችን ላይ ከፍተኛ ወጪ ከወጣባቸው ግብዣዎች በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ለሰርጉ የወጣው አጠቃላይ ወጪም 70 ሚሊዮን ዶላር ነው።

2.  የታይኮን ላክሺኒ ሚታል ልጅ ሰርግ

ህንዳዊው ላክሼኒ ሚታል የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ባለቤት ሲሆኑ በሀብት ደረጃም ቢሊየነር ናቸው። እኚህ ሰው ሴት ልጃቸውን በ2004 ሲድሩ የደገሱት ድግስ በድምሩ 60 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል። የሰርግ መጥሪያ ወረቀቱ በብር የተለበጠ እና 20 ገፆች ያሉት ነበር። ከመላው ዓለም በሰርጉ ላይ እንዲታደሙ የተጠሩት እንግዶች በአጠቃላይ በፓሪስ እና ዙሪያዋ ባሉ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል እንዲያርፉ ተደርጓል። በተጨማሪም ሰርጉን ለማድመቅ ከኤፍል ታወርስ ላይ ርችት ተተኩሷል። ለሰርጉ የቀረበው የወይን ጠጅም 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ሲሆን፤ ለግብዣውም ከመቶ በላይ የምግብ አይነቶች ተዘጋጅተው ነበር፡

3.  የዱባዩ ንጉስ ሰርግ

ንጉስ ሼክ ሞሐመድ ቢን ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ኖህያን እ.ኤ.አ. በ1981 ንግስት ሰላማን ሲያገቡ በአጠቃላይ 45 ሚሊዮን ዶላር ለሰርጉ ወጪ ተደርጎ ነበር። ለሰርጉ ተብሎ የተገነባው ስታዲየም 20ሺህ ሰዎችን የመያዝ አቅም ነበረው። ለንግስቲቱ የተላኩት ስጦታዎች በ20 ግመሎች ላይ የተጫኑ ሲሆን፤ ግመሎቹም በብር ጌታጌጥ ያሸበረቁ ነበሩ።

4.  የአትላንቲስ ሆቴል መክፈቻ ዝግጅት

አትላንቲስ ሆቴል በዱባይ ፓልም ደሴት ላይ በሰው ልጅ ድንቅ ጥበብ ከተሰሩ ሆቴሎች ቀዳሚው ነው። ይሄ ሆቴል በሚመረቅበት እለት በርካታ ትላልቅ የዓለማችን ድምጻዊያን ተገኝተው ያቀነቀኑ ሲሆን፤ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ርችቶች ከሰማይ ላይ ተተኩሰዋል። በአጠቃላይ 2ሺህ ታዋቂ ታዳሚዎች የተገኙ ሲሆን፤ በአጠቃላይም 31 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል።

5.  የብራኒ ሱልጣን ልደት

ብራኒ የዓለማችን ትንሽ ሀገር ብትሆንም በነዳጅ ሀብቷ ግን ታዋቂ ናት። የሀገሪቱ ሱልጣን ታዲያ 50ኛ ዓመት ልደታቸውን በሚያከብሩበት ወቅት ከፍተኛ ወጪን አውጥተዋል። እኚህ ሱልጣን በ1996 እ.ኤ.አ. 50 ዓመታቸውን ሲያከብሩ የሀገሪቱ የመንግስት ሠራተኞች ክፍያቸው በ20 ዓመታት ወስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲጨምር ተደርጓል። በዝግጅቱ ላይም ማይክል ጃክሰን ዘፈኑን ያቀረበ ሲሆን፤ በርካታ ታዋቂ ሰዎችም ተገኝተው ነበር። በአጠቃላይ ለልደት ማክበሪያው 27 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጓል።

6.  የኤልዛቤት ብሩክስ ልደት

ዴቪድ ብሩክስ የጦር መሣሪያዎችን በመስራት ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን በሀብት ደረጃም የናጠጡ ናቸው። እኚህ ሰው ኤልዛቤት የተባለችው ሴት ልጃቸው 13ኛ ዓመት ልደቷን ስታከብር 10 ሚሊዮን ዶላር የፈጀ ዝግጅት ነበር የተዘጋጀላት። በዝግጅቱ ላይ ፊፍቲ ሴንትን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ አቀንቃኞች ተገኝተው ዘፈናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ በአባቷ የግል ጀትም ተንሸራሽረዋል።

7.  የዋይኒ ሩኒ ሰርግ

የእግር ኳስ ኮከብ ዋይኒ ሩኒ እና የኮሊን ማክላግሊን ጋብቻ የተከናወነው በ17ኛው ክፍለ ዘመን በነበረ ፋሽን በተሰራ ቪላ ቤት ነው። ሰርጉ እጅግ የተቀናጣ በመሆኑ በአጠቃላይ 8 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል።

8.  የዴቪድ ቦደርማን ልደት

ቦደርማን የቴክሳስ ፓሲፊክ ግሩፕ መስራች ናቸው። ሰውየው በአሜሪካ ከሚገኙ ባለፀጎች አንዱ ሲሆኑ አጠቃላይ ሀብታቸውም 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ነው። እኚህ ሰው ልደታቸውን ለማክበር 7 ሚሊዮን ዶላር አውጥተዋል።

9.  የቢል ክሊንተን ልጅ ሰርግ

የፕሬዝዳንት ክሊንተን ልጅ የሆነችው ቸልሲ ክሊንተን ስታገባ የተዘጋጀው ኬክ ብቻ 11ሺህ ዶላር ዋጋ ያለው ነበር። በሰርጉ ላይ 500 እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ለሰርጉ የወጣው ወጪ 5 ሚሊዮን ዶላር ነበር።

10.   የሊዛ ሜኔል ሰርግ

የጁዲ ጋርላንድ ልጅ የሙዚቃ ባለሞያውን ዴቪድ ገስትን ስታገባ 60 የሙዚቃ ኦርኬስትራ ቀርቧል። በሰርጉ ላይ ስቲቭ ዎንደርን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ አቀንቃኞች የተገኙ ሲሆን፣ ማይክል ጃክሰንም የወንድ ሚንዜ ነበር። ኤልዛቤት ቴይለርም የሙሽራዋ ስርሚዜ ነበረች። ሰርጉ በአጠቃላይ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
244 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 880 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us