ታሪክ የማይረሳቸው ውድ ስጦታዎች

Wednesday, 11 October 2017 13:09

 

ባለፈው ሳምንት በዓለማችን ላይ ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶባቸው የተከናወኑ ግብዣዎችን (party) ከሞላ ጎደል ገልፀን ነበር። ዛሬ ደግሞ በዓለማችን ታሪክ ከፍተኛ ገንዘብ የወጣባቸውን አንዳንድ ስጦታዎች እንጠቃቅሳለን። አብዛኞቹ ስጦታዎች የሚዋደዱ ሰዎች እርስ በርስ ተሰጣጧቸው ሲሆኑ፤ ጥቂቶቹ ደግሞ ጠቢባን ለዚህች ዓለም ያበረከቷቸው ስጦታዎች ናቸው።


1. አብራሃሞቪች የነሃስ ቅርፅ


የአለማችን ቱጃሩ ሮማን አብርሃሞቪች ለፍቅረኛው ያበረከተላት ከነሀስ የተሰራ ቅርፅ ዋጋው 14 ቢሊዮን ዶላር ነው። ይሄ ብቻም ሳይሆን ሰውየው ለፍቅረኛው በርካታ ውድ እና ውብ ስዕሎን በስጦታ መልክ ያበረከተላት ሲሆን፤ ዋጋቸውም በድምሩ 120 ሚሊዮን ዶላር ነው።

 

2. የሻሩክ ካን ስጦታ


ታዋቂው ህንዳዊ የፊልም ተዋናይ ሻሩክ ካን አር ኤ ዋን በተባለው ፊልም ላይ ተሳትፎ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል። በመሆኑም ይሄንን ተቀባይነት ማግኘቱን ምክንያት በማድረግ በፊልሙ ላይ ለተሳተፉ አባላት ውድ የሆኑ ቢ ኤም ደብል ዩ 7 መኪናዎችን በስጦታ መልክ አበርክቷል። ለአባላቱ የተበረከቱት መኪናዎች እያንዳንዳቸው 10 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ አላቸው። ይህ ስጦታ በውድነቱ ብቻም ሳይሆን በአንድ ጊዜ ለበርካታ ሰዎች የተሰጠ ውድ ስጦታ በመሆኑ በታሪክ ውስጥ ተመዝግቦ ተቀምጧል።

 

3. የቡርጅ ከሊፋ 19ኛ ወለል


በታዋዊው የዱባይ ቡርጅ ከሊፋ ላይ የሚገኘው 19ኛው ወለል በዓለማችን ላይ እጅግ ውድ ከሆኑ ወለሎች ተርታ የሚመደብ ነው። ራጅ ኩድራ የተባለው ሰው ታዲያ ሺልፓ ሼቲ ለተባለችው ሚስቱ ይሄንን ወለል በስጦታ መልክ አበርክቶላታል።

 

4. የ60 ሚሊዮን ዶላር ጀት


የአምባኒ ቤተሰብ በህንድ ሀገር ከሚታወቁ ባለፀጎች ቀዳሚዎቹ ናቸው። ይሄንን ሀብታቸውን ለማሳወቅ አልባኒ ለሚስቱ ኒታ አልባኒ የ60 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ጀት በስጦታ መልክ አበርክቶላታል። ጀቱም በውስጡ የሙዚቃ ሲስተም፣ መጠጥ ቤት፣ ማብሰያ ክፍል እንዲሁም መታጠቢያ ቤት ያለው ቅንጡ ጀት ነው።

 

5. የ85 ሚሊዮን ዶላር ጀልባ


አኒል አምባኒ የተባለው ሌላ ህንዳዊ እጅግ ለሚወዳት ሚስቱ ቲና የ84 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የሽርሽር ጀልባ ገዝቶ አበርክቶላታል።

6. የቴይለር ዳይመንድ


ኤልዛቤት ቴይለር በህይወት ዘመኗ በርካታ ውድ ስጦታዎችን ስትቀበል እንደኖረች ይታወቃል። ከእነዚህ ውድ ስጦታዎች ሁሉ የላቀው እና እስከ አሁንም ዝናው የሚነገረው የቀድሞ ባለቤቷ ሪቻርድ በርተን ያበረከተላት ስጦታ ነው። በርተን ኤልዛቤት በ1997 (እ.ኤ.አ.) 40 ዓመቷን ስታከብር 69 ነጥብ 42 ካራት ዳይመንድ በስጦታ ሰጥቷታል። የዳይመንዱ ዋጋም 1 ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ነበር።

 

7. የባራክ ኦባማ ስጦታ


ወደ ቅርብ ጊዜ ስንመጣ ደግሞ የአሜሪካ ቀድሞ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከንጉስ አብዱላህ የተቀበሉት ስጦታ ይጠቀሳል። ኦባማ ከንጉስ አብዱላህ የተለያዩ የከበሩ ድንጋዮች፣ የወርቅ ጌጣጌጦች እንዲሁም ዳይመንድ የተቀበሉ ሲሆን አጠቃላይ ዋጋቸውም 300 ሺህ ዶላር ነው።


8. ታጅ ማሃል


ህንዳዊው ሻይ ጃን በሞት የተለየችውን ባለቤቱ ሙንታዝ ማሃልን ለማስታወስ ሲል ያስገነባው ታጅ ማሃል በዓለም ላይ ታዋቂ ከሆኑ ግንባታዎች ተጠቃሽ ነው። ይህ የእውነተኛ ፍቅር መገለጫ ተብሎ የተሞካሸ የቀብር ቦታ የተገነባውም በ38 ሚሊዮን የህንድ ሩፒ ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
496 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 923 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us