አውሮፕላን ባለመስራታችን አንፀፀት

Wednesday, 11 October 2017 12:35

“ለብዙ ዘመናት የምድር አማልክት ጦር እንደ ችቦ ሲናጠቁብን ኖረዋል። ለፈጠራ እና ለሳይንስ ፋታ አልነበረንም፣ ቢሆንም የመለወጥን ሕግ (ሜታሞርፎሲስን) ተከትለን የሳይንስ ባለቤቶች ያቃታቸውን ሞክረናል። አንድ ቀን ገጠር ወርጄ ሴቶች ከወደቀ የመድፍ ቀለሕ የቡና ሙቀጫ ሰርተው ቡና ሲወቅጡ አይቼ እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ። የመገለጥ እንባ ነበር። አውሮፕላን ባለመሥራታችን ኮምፒዩተር ባለመፈልሰፋችን መፀፀት አይገባም አልሁ። አየህ፣ አውሮፕላን መሥራት ኮምፒዩተር መፈልሰፍ ሰውን የተሻሻለ አላደረጉትም። በምንጅላቶቻችን ዘመን የነበረውን ክፋት፣ ሞት እና ሽብር አልገሩትም። የመድፍ ቀለሕን የቡና ሙቀጫ አድርጎ መቀየር ግን፣ የሞትን ዕቃ ወደ ህይወት ዕቃነት ማሸጋገር ነውና ቀላል ግኝት አይደለም።

 

“ወደፊት አንድ ቀን ወይ ጎበዝ ሽፍታ አልያ ጎበዝ ተመራማሪ ወይ ጎበዝ ባል እንደምሆን ጥርጥር የለኝም። ብቻ የሆነ የላቀ ብቃት ሳላሳይ የካፌው ትውልድ አንድ አባል ሆኜ ብቻ ማለፍ አልፈልግም። አሁን ብዙ የምፈልጋቸውን ነገሮች በዕድልም በለው በትግል አግኝቻለሁ ሥራ ማግኘት እፈለግ ነበር አግኝቻለሁ፤ ለዚያውም በአንድ NGO (Non Growth Organization) ውስጥ እሰራለሁ። መሥሪያ ቤታችን እከክ ላስቸገራቸው አካባቢዎች ልብስ እና ሳሙና አያቀርብም፤ ከዚያ ይልቅ እከክ ላስቸገራቸው አካባቢዎች የማከኪያ ማሽን ያቀርባል። የነገርኩህን ባታምን አይገርመኝም። የውጭ አገር ሰው መሆን ገደብ የለሽ መብት እንደሚያጎናጽፍ አታውቅም። ኢትዮጵያዊ ከአገሩ የሚወጣው ለምንድን ነው? የውጭ አገር ሰው ሆኖ ለመመለስ ነው። የውጭ አገር ሰው ሆኖ ሲመጣ በተወላጅነቱ ያላገኘውን መብት ያገኛል።


አንድ የሰፈራነችን ሽማግሌ መሬት ለመግዛት ጠየቁ - ጉለሌ። በካሬ ሜትር የተጠየቁት ገንዘብ ቢያስደነግጣቸው፤ “የጉለሌ መሬት ዑራኒየም አለው እንዴ!!” ብለው ባለ ሥልጣኑን ጠየቁት። ግን በጣም ሰፊ ከመሆኑ የተነሣ ወንዝ እና ተራራ ቢገጠምለት “አገር” ተብሎ በተ.መ.ድ ምክር ቤት ዕውቅና ይሰጠው ነበር። በዚህ ረገድ በምሥራቅ በኩል ኢትዮጵያን ሶስት አገሮች ያዋስኗታል - ሶማሊያ፣ ጅቡቲ እና የጅቡቲ ኤምባሲ”።
(መግባትና መውጣት፤ በእውቀቱ ስዩም)

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
195 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 944 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us