ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ

Wednesday, 22 November 2017 12:12

 

ቀጣዮቹ ወራት በሃገራችን የሰርግ ስነስርዓት በስፋት ከሚካሄድባቸው ወራት የሚመደቡ ናቸው። እኛም ለዛሬ በዓለማችን ላይ ለየት ያለ ባህል የሚከናወንባቸውን የሰርግ ሥነ-ስርዓቶች እንቃኛለን። አንዳንዶቹ ምክንያታዊ ቢሆኑም ሌሎቹ ግን ለምን እንደሚተገበሩ እንኳን አይገባም።

-    በኮንጎ ሙሽሮች በሰርጋቸው ስነሥርዓት ላይ ፈገግ ማለት አይፈቀድላቸውም። ፈገግ ካሉ ግን ጋብቻውን እንደ ቁምነገር አልወሰዱትም ይባላል።

-    በሞሪሽየስ ችቦ አይሞላም ወገቧ የሚለው ዘፈን ለሙሽሪት አስፈላጊ አይደለም። ይልቁንም ሙሽሪት እስከ ዕለተ ሰርጓ ድረስ ሰውነቷ ወፍራም እና ግዙፍ እንዲሆን የቻለችውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅባታል። ሙሽሪት እየወፈረች በሄደች ቁጥር ሀብታም የመሆን እድሏ ይጨምራል ተብሎ ይታሰባል።

-    በሞንጎልያ ደግሞ ጥንዶቹ ጋብቻ ከመፈለጋቸው በፊት ዶሮ ገድለው በመገነጣጠል ጤናማ የሆነ ጉበቱን ማውጣት አለባቸው።

-    በተወሰኑ የህንድ ጎሳዎች ዘንድ ሴቶች ቀጥታ ጋብቻ ከመፈፀማቸው በፊት ከዛፍ ጋር እንዲጋቡ ይደረጋል።

-    በደቡብ ኮሪያ ባህላዊ መንገድ የሚያገባ ጉብል ከሰርጉ በፊት የሚመጣውን ቅጣት መሰል ድርጊት መታገስ አለበት። ይኸውም የሙሽራው ቤተሰቦች እና ጓደኞቹ የቻሉትን ያህል ውስጥ እግሩን እንዲገርፉት ማድረግ እና ግርፋቱንም መታገስ ነው።

-    በአርሜኒያ ጋብቻ ለመመስረት እና ጎጆ ለመያዝ የሚፈልጉ ወጣቶች ከሰርጉ ቀን ቀደም ብለው ጨው የበዛበት ዳቦ ይመገባሉ። ይሄ ዳቦ መካከለኛ እድሜ ባላት እና በደስተኛ ሴት እንዲጋገር ተደርጎ የሚበላ ሲሆን፤ ይሄን የሚያደርጉትም ስለ ትዳር አጋራቸው ተስፋ ሰጪ ህልም ለማለም ነው።

-    በፈረንሳይ ደግሞ አንድ ባህል አለ። ሙሽሮች በሰርጋቸው ዋዜማ ቸኮሌት እንዲመገቡ እና ሻምፓኝ እንዲጠጡ ይደረጋል። አሳዛኙ ነገር ግን እነዚህን ነገሮች እንዲመገቡ የሚደረገው ለሽንት ቤት ከተዘጋጁ ጉድጓዶች ውስጥ መሆኑ ነው። እንዲህ የሚደረገውም ጥንዶቹ በቀጣይ በጋብቻቸው ፅናት ያላቸው እንዲሆኑ ነው።

-    በቻይና ባህላዊ የጋብቻ ስነስርዓት ደግሞ ሙሽራው በተደጋጋሚ ሙሽሪትን በቀስት መምታት ይጠበቅበታል። ደጋግሞ ከመታት በኋላ ቀስቶቹን ሰብስቦ በሰርግ ስነሥርዓቱ ላይ ይሰባብራቸዋል። ድርጊቱን የሚፈፅመውም ፍቅራቸው ዘላለማዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።

-    በሩሲያ ባህላዊ የሰርግ ስነሥርዓት መሠረት ጥንዶች መጋባት ከወሰኑ በኋላ ሙሽራው በሰርጉ እለት ማለዳ ላይ ወደ ሙሽሪት ቤተሰቦች ቤት በማምራት ያለውን ታማኝነት መግለፅ ይኖርበታል። ሙሽራው ለአማቾቹ የተለያዩ ስጦታዎችን ማበርከት ካልሆነም ጋብቻውን እሺ እስከሚሉት ድረስ መዝፈን ይጠበቅበታል።

-    በቻይና ቱጂአ ጎሳዎች ዘንድ ያለው ባህል ደግሞ ማልቀስ ነው። ሙሽሪት ከሰርጓ አንድ ወር ቀደም ብላ በየእለቱ ለአንድ ሰዓት ማልቀስ ይጠበቅባታል። ከአስር ቀናት በኋላ ማልቀሱን እናቷም የምታግዛት ይሆናል። በቀጣዮቹ አስር ቀናት ውስጥ ደግሞ ሴት አያት ካለቻት እርሷም አብራቸው ታለቅሳለች። ወሩ ሲጠናቀቅም በቤተሰቡ ውስጥ የሚገኙ ሴቶች በአጠቃላይ ከሙሽሪት ጋር ያለቅሳሉ። ሴቶቹ የተለያዩ ዜማዎችን እና ድምጾችን እያወጡ ስለሚያለቅሱ የደስታ መግለጫ ተደርጎ ይወሰዳል። 

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
197 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 919 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us