ዝሆኗ የሳለቻቸው ስዕሎች ለጨረታ ቀረቡ

Wednesday, 22 November 2017 12:20

 

በሀገረ ሃንጋሪ ሰሞኑን የተሰማው ወሬ እንስሳት የደረሱበትን ደረጃ ያመለክታል። ሮይተርስ እንደዘገበው ህንዳዊቷ የ42 ዓመት እድሜ ያላት ዝሆን፤ ሳንድራ፤ በተለያዩ ጊዜያት የሰራቻቸው ስዕሎች በሀንጋሪ ለጨረታ ቀርበዋል። በሳንድራ የተሰሩት ሶስት ስዕሎች እያንዳንዳቸው 150 ዶላር ዋጋ እንደተሰጣቸውም ተገልጿል። ሳንድራ ቀደም ብላ ብሩሽን እንደ ልቧ መጠቀም የለመደች ስትሆን፣ አሁን ደግሞ አስገራሚ የሆነ ስዕሎችን በኩምቢዋ በሸራ ላይ ሰርታለች። ሳንድራ እንደሌሎች ዝሆኖች ተገዳ ወይም በማባባል የምትስል ሰዓሊ ሳትሆን፤ ደስ የሚል ስሜት ሲሰማት በራሷ ጊዜ ስዕሎችን አስውባ የምትስል ናት ተብሏል። የፈረስ አክሮባትና ሰርከስ ዳይሬክተር የሆነው አሳዳጊዋ ፍሎሪያን ሪፑር እንደገለፀውም በራሷ ተነሳሽነት ስዕሎችን ስትስል በቃላት እደሚያበረታታት ተናግሯል። ከሳንድራ ጋር 40 አመታትን አብረው እንዳሳለፉ የተናገረው አሳዳጊዋ፤ ስዕሎቿን ስትስል ብሩሾችን በመቀየር እና በማቀራረብ ብቻ እንደሚያግዛት ተናግሯል። ሳንድራ ቀድሞ በሰርከስ ስራ የሰለጠነች ስትሆን አሁን ደግሞ በሰአሊነቷ አለም አውቋታል። ስዕሎችን የምትስለውም እንደመዝናኛነት መሆኑን ያስነበበ ዘገባው በሀንጋሪ ለጨረታ የቀረቡት የሳንድራ የስዕል ውጤቶች ተሸጠው የሚገኘው ገቢ በማሌዝያ ለሚገኝ የዝሆኖች መጠለያ በስጦታ መልክ ይበረከታል ሲል ጨምሮ አትቷል።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
174 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 850 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us