የሴቶች ውጤቶች

Wednesday, 06 December 2017 13:11

 

እንዲህ እንደዛሬው ሴቶች በአደባባይ ሳይውሉ እና ከወንዶች እኩል በእውቀት ገበታ ላይ ሳይሰለፉ በራሳቸው ተነሳሽነት አለምን የለወጡ ድንቅ ፈጠራዎችን ለአለም ያበረከቱ የሰው ልጆች ባለውለታዎች አሉ። እኛም ለዛሬው በፈጠራቸው የሰውን ልጅ ህይወት እስከመታደግ የደረሱ ምርጥ የፈጠራ ባለሞያ ሴቶችን እናቀርባለን።


የህክምና ሲሪንጅ፡- አሁን ያለውን እና በአንድ እጅ በመጠቀም አገልግሎት ላይ ሊውል የሚችል የህክምና ሲሪንጅ በመፍጠር በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የማይተካ ሚናን የተጫወተችው ሴት ሌቲቲያ ጊር ትባላለች። ይህች ሴት ቀደም ሲል ሀኪሞች በሁለት እጆቻቸው ይዘው ይወጉበት የነበረውን ሲሪንጅ ሊተካ የሚችለውን ሲሪንጅ የፈጠረችው እ.ኤ.አ. በ1891 ዓም ነበር።


ዘመናዊ ማቀዝቀዣ (ፍሪጅ)፡- በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራው ዘመናዊ ማቀዝቀዣ የተፈጠረው እ.ኤ.አ በ1914 ዓ.ም ሲሆን፤ የፈጠራው ባለቤት ደግሞ ፍሎረንስ ፓርፓርት ትባላለች። ይህች ሴት ፈጠራዋ በዚህ ብቻ ያበቃ ሳይሆን በ1960 የአደባባይ መንገዶችን የሚያፀዳ ማሽን ፈጥራ ለአሜሪካ ገበያ በማቅረብ እውቅናን አግኝታለች።


የደህንነት ካሜራ፡- ይህንን ካሜራ በመፍጠር እውቅናን ያገኘችው ሴት ሜሪ ቫን ብሪታን ትባላለች። ሜሪ ይህን ካሜራ የፈጠረችው በ1969 ዓ.ም ሲሆን፤ ምክንያት የሆናትም እርሷ በምትኖርበት ኒውዮርክ እና አጎራባች ከተሞች ሰዎች ችግር ገጥሟቸው ለፖሊስ ሲያሳውቁ ፖሊስ በአፋጣኝ መድረስ ስለማይችል ካሜራዎቹ እገዛ እንዲያደርጉ መፈለጓ ነበር።


የእሳት አደጋ ማምለጫ፡- በማንኛውም የእሳት አደጋ ሊከሰትበት በሚችል ቦታ ሊያገለግል እና የሰዎችን ህይወት ሊታደግ የሚችለው የእሳት አደጋ ጊዜ ማምለጫ መሳሪያ የተፈጠረው በ1887 ዓ.ም ሲሆን፤ የፈጠራው ባለቤትም እና ብኔሊ ትባላለች።


የቡና ማሽን፡- አሁንም ድረስ አለማችን እየተገለገለበት ያለው የቡና ማፍያ ማሽን የተፈጠረው በ1908 ሲሆን፤ ፈጣሪዋ ደግሞ አንዲት የቤት እመቤት ናት። ሜሊታ ቤንክ የተባችው ጀርመናዊት የቤት እመቤት የቡና ማፍያ ማሽን አሁን ያለውን ይዘት እንዲኖረው አድረጋ ከመስራቷ በፊት ሰዎች የተፈጨ ቡናን በስስ ጨርቅ ቋጥረው በማንቆርቆሪያ ውስጥ በማፍላት ይጠቀሙ ነበር።

 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
125 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 911 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us