የትራፊክ መስመር ቀያሪው

Wednesday, 06 December 2017 13:16

 

ስልጣኔና ቴክኖሎጂ ያስገኙልን በርካታ ነገሮች አሉ። እነዚህ ግኝቶች በአብዛኛው የሰውን ልጅ ህይወት ቀላል የማድረግ ጠቀሜታ ያላቸው ሲሆን፤ የአጠቃቀማችን ሁኔታ ከጥቅማቸው ጉዳታቸው እንዲያመዝን ያደርገዋል። የዚህ ውጤት ይመስላል አንዱን ቻይናዊ ለቅጣት የዳረገው። ሞደርስን ኤክስፐረስ የተባለውና የሀገሪቱን ዜና አውታር ጠቅሶ ዩፒአይ ሰሞኑን ያስነበበው ዜና የቸገረው እርጉዝ ያገባል ሳያስብል ይቀራል?


ነገሩ እንዲህ ነው። ሳይ የተባለው የ28 ዓመቱ ቻይናዊ በመኪና መንገድ ላይ ትራፊክ ፖሊስ ያስቀመጠውን መስመር ለራሱ እንዲመቸው አድርጎ ሰርቷል በሚል ነው የተፈረደበት። ሳይ ትራፊክ ፖሊስ ያሰመረውን መስመር ለራሱ በሚመቸው መልኩ አቅጣጫ እየቀየረ ሲያሰምር በተቆጣጣሪ ካሜራ ሊያዝ ችሏል። ሳይ ከትራፊክ ፖሊስ ቀለም ጋር ተመሣሣይ የሆነ ነጭ ቀለምን በመጠቀም የትራፊክ ዝውውሩን አስተጓጉሎ በመገኙቱ ነው የሊያንያንግ ጀያንግሱ ግዛት ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው። ሳይ ለፖሊስ እንደተናገረው ከሆነም ይሄንን ያደረገው በየዕለቱ ወደ ስራ ለመሄድ የሚገጥመውን ረጅም ጊዜ የፈጀ ጉዞ ለማስቀረት በማሰብ ነው።


ሳይ ለፖሊስ ሲናገርም “እንደተመለከትኩት ከሆነ ቀጥታ የሚያሳልፈው መስመር ሁልጊዜም በመኪኖች የተጨናነቀ ሲሆን፤ ወደ ግራ የሚያሳጥፈው መንገድ ግን ብዙ ክፍት ቦታ አለው። ስለዚህ መስመሩን ብቀይረው የእየእለት ጉዞዬን ቀላል ያደርግልኛል” ብሏል። ሳይ በሰራው ስራ ብዙ ትርምስ እና ግጭት መፈጠሩን የገለፀው ትራፊክ ፖሊስ፣ ለዚህ ጥፋትም ሳይ በአንድ ሺህ የን ወይም በ151 ዶላር እንዲቀጣ ወስኖበታል። በቻይና ለራሱ የሚመቸውን መስመር በመስራት ለቅጣት የተዳረገው ሳይ ብቻ አለመሆኑን የገለፀው ዘገባው፤ ባለፈው ግንቦት ወር ላይ አንድ ግለሰብ ለራሱ የሚያመቸውን የመኪና ማቆሚያ መስመር በጠመኔ (ቾክ) ሲያሰምር በካሜራ ቁጥጥር ስር ውሎ ለቅጣት መዳረጉን አስታውሷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
177 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 933 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us