የጦጢት ፍርድ

Wednesday, 20 December 2017 12:56

 

አንድ ተኩላ አንዱን ቀበሮ “ንብረቴን ሰርቀህብኛልና ክፈል” አለው። ቀበሮውም “ፈፅሞ አልወሰድኩብህም ይህንን ሁሉ የምትለው ከኔ ሌላ ነገር ስለፈለግህ ነው” ሲል መለሰለት። “ወስደሀል” “አልወሰድኩም” እሉ ብዙ ሲከራከሩ ለመግባባት ባለመቻላቸው ጦጢት በፕሬዚዳንትነት ወደምትመራው ፍርድ ቤት ሄዱ።

እዚያም እንደደረሱ ተኩላ “ይኽውና አቶ ቀበሮ ንብረቴን ሰርቆብኛልና ይመልስልኝ” ሲል ክሱን አሰማ።

ቀበሮም “አልወሰድኩም እኔ ምንጊዜም ታማኝ ፍጡር እንጂ ሌባ አይደለሁም በማለት መልስ ሰጠ።

ከዚያም በፍርድ ቤቱ የነበሩት ሁሉ ተኩላውም ንብረት ተወስዶበት እንደሆነና ቀበሮውም ሰርቆ እንደሆነ ለማወቅ በርካታ መስቀለኛ ጥያቄ መልስ ይሰጡ ነበር።

የሚሰጡት መልስም ተመዝግቦ ለፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ለወ/ት ጦጢት ተሰጠ።

እሷም ሁሉን መረመረችና “በእውነቱ አቶ ተኩላም እቃ ተወስዶብኛል ላልከው ሌላ ምክንያት ቢኖርህ እንጂ አልተወሰደብህም። አቶ ቀበሮም ለተጠየከው ጥያቄ ሁሉ አላውቅም ብለህ ከመመለስህም በላይ ሌባ ለመሆን ብዙ ማስረጃ ቀርቦልሃልና በወንጀል ትጠየቃለህ።” ብላ ፈረደችበት ይባላል።

                     የኦዞ ተረቶች - በተሾመ ብርሃኑ 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
120 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 964 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us