ወጣቱ ስብሐት

Wednesday, 20 December 2017 12:57

 

… “ወጣቱን ስብሐት ለማግኘት ከርባ-ገረድ መውጣት ሊኖርብን ነው። ትንሹ ስብሐት መተኛት የሚወድ ሆነ። መኝታ የሚበዛበት አኗኗር ደግሞ ለርባ-ገረድ አይስማማትም። ስለዚህ እናቴ መከረችኝ። አዲስ -አበባ ነው የሚስማማህ፣ እዚያ እንደ እናት ሆኜ ያሳደኩት ወንድሜ አለ። ሂድ ያኖርሃል አለችኝና መጣሁ። ያኔ አሥር ዓመት ቢሆነኝ ነው። እውነትም አጎቴ ጋሼ ሐጎስም ተቀበለኝ። ሽሮ ሜዳ አካባቢ ስዊድሽ ሚሽን ትምህርት ቤት ገባሁ።

“እዚህ ላይ የእናቴ የፍቅር ተፅዕኖ መሠረቱን ጥሎ ገለል የሚልበት ጊዜ ደረሰ ማለት ነው። ለአዲስ አበባ አዲስ ነኝ። ርባ-ገረድ የተገነባው በራስ መተማመን እዚህ ጥርጣሬ ላይ ይወድቅብሃል። ባላገር ነው ብለው ይንቁኛል ብዬ በማስብበት ወቅት አንዲት አባባሽ ሴት መጣችና ትሬንታ ኳትሮ የዳጠው ነው የሚመስለው አፍንጫህ አለችኝ። በቃ አስቀያሚ እንደሆንኩ ነው የሚመስለኝ። በኋላ ከእለታት አንድ ቀን ደግሞ የልባችንን መሰበር ያዩ አማልክት ሌላ ሴት ላኩ። ‘አንተ! እንዴት ነው ስትስቅ! አይንህ ያበራልን‘ኮ’ ስትለኝ በቃ ዳንኩ።

“አየህ፤ ከእናት ቀጥሎ የሌሎችን ሴቶች አስተያየት የምናፍቅበት ዕድሜ ላይ ደረስኩ ማለት ነው። ወጣትነት ሲያቆጠቁጥ። አጎቴ የኢትዮጵያ መንግሥት በግሪክ ሌጋሲዮን አማካኝነት ተሹሞ ሲሄድ ጃንሆይ እኛን ተፈሪ መኮንን አዳሪ ትምህርት ቤት አስገቡን። ወጣትነት ጡንቻ አውጥቶ ወደ ኮረዶች ይገፋፋን የጀመረው ከዚህ በኋላ ነው።”

 

ተለዋዋጩ የሕይወት ገፅታ ቀጠለ?

“ምን አይነት ጥያቄ ነው? ድሮ ሊቆም ፈለክ? ቀጠለ’ንጂ። ልጅ ሆነህ የምታውቃት ሴት እናትህ ብቻ ናት። እዚህ የወጣትነት ደረጃ ላይ ስትደርስ ሌላ ተጨማሪ ሴት ታስፈልግሃለች። ያቺ ሴት ደግሞ እናትህ ልጅነትህን በፍቅሯ ጠቅልላ እንደገዛች ወጣትነትህ የዚች ይሆናል። አነሰም በዛም እናትህ ልጅነትህን በገዛችበት መንገድ ነው ለዚች ሴት የምትንበረከከው። የእኔ እናት ወለላይ በፍቅር አይደል ያሳደገችኝ? ቀጣይዋ ሴት ከኔ ጉዳት አይደርስባትም። እንደውም እኔን የሚያዝዙኝ እነሱ (ሴቶቹ) ናቸው። እናቴ እኔ ላይ የነበራትን ሥልጣን ነው ያስረከብኳቸው። ሚስቶቼም ይሁኑ ዝም ብሎ ራቅ ያለ ፍቅረኞችም ይሁኑ እንደፈለጉ ነው የሚነዱኝ። ሲፈልጉ ሲኖራቸው ያለብሱኛል፣ ያስዘንጡኛል። እኔ ብቻ ያለኝን ገንዘብ ሰጥቼ የለሁበትም። ሁልጊዜም ሴትዬዋ ውስጥ እናት አለች። ልጄም እንኳን እናት የምትሆንበት ጊዜ አለ…”

           ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ህይወትና ክህሎት - በአለማየሁ ገላጋይ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
128 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1066 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us