የማይረባ ብዕር

Wednesday, 03 January 2018 16:55

 

አደራውን ክዶ ብዕር ከሸፈተ፣
የሀቅ ነቁጡን ስቶ ዘሩን ከጎተተ።
ከዓላማው ተጣልቶ ሚዛኑን ካደፋ፣
ስልጣኑን ሊያመቻች ቀለሙን ከደፋ።
ዘረኛ ሊዋጋ ዘረኛ ከሆነ።
ሚዛኑን ካደፋ ምኑን ብዕር ሆነ?
ዕውነቱን ለጥቅሙ ደልዞ ከጻፈ፣
ቀስጦ ወስልቶ ክብሩን ከገፈፈ።
መልኩ ያለየለት ባሕሪው ብልጭልጭ፣
ይህን መሳይ ብዕርስ ቢሰብሩትም አይቆጭ።
ተግባሩን ዘንግቶ ብዕር ከዘመመ፣
ድግስ ባየ ቁጥር ሲያኳስ ከከረመ፣
ኅሊናውን ሽጦ ስሙን ከቀየረ፣
ምኑን ብዕር ሆነ ጌታዳር ካደረ፣
ዘረኛን አጋልጦ ከህዝብ ካልወገነ፣
ዲያቢሎስ ነው እንጂ ምኑን ብዕር ሆነ!
ጠበቃ የማይሆን ነገ ተከሳሽ ነው፣
ጽፎ ካላዳነ ሰባብሮ መጣል ነው።
በጨለማው መርፌ ከሩቁ ሲታየው፣
በቀን ዝሆን ቆሞ መች በቅጡ ለየው?
ሲደማ ካልታየ በዕውን ለእውነት፣
በእሳት ማጋየት ነው ብዕር ያበለ ለት።
ትናንት ከጻፈለት ከቃኘው ዕውነታ፣
ዛሬ ባዲስ አቋም ልቡ ካመነታ።
ነገር የቀበሮ ልቡን ከሰረቀው፣
ይዋል ይደርና ታሪክ ይጠይቀው።
ልፋፌ ክታቡ ሀቅ የለውምና፣
ይረገም ይወገዝ “ብዕር” ቀረ መና።
የሀቅ አብነቱ ገጹ ከጠፋበት፣
ብዕር ድንጋይ አይቶ “ዳቦ ነው” ያለ ዕለት።
ወገኑ ሲቃጠል ሲጮህ ከሩቅ አይቶ፣
ካላንገበገበው ጢሱ ባ’ይኑ ገብቶ።
ግፍና በደልን ደፍሮ ካልገዘተ፣
ሀቅ ይነቀኝ ብሎ ለእውት ካልሞተ፣
ከጦር ሰባቂ ጋር ከተጎራበተ፣
መቃ ብዕርም አይደል፣ እሱስ መቃብር
ነው ቀለሙን የደፋ፣
ሥጋ ደሙ ሸቶ በቁም የከረፋ።

 

ብዥታ - ስብሰብ ግጥሞች- በአስማማው ኃይሉ (አያ ሻረው)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
107 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1078 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us