የወንዝ ላይ የመጠጥ መደብ

Wednesday, 03 January 2018 16:58


የኒው ዚላንድ መንግስት በየአመቱ አዲስ አመት በተቃረበ ቁጥር በአደባባይ የአልኮል መጠጦች እንዳይጠጡ እገዳ ያደርጋል። የእገዳው መነሻም አዲስ አመትን ለማክበር እየተባለ ብዙ አልኮልን በመጠጣት የሚፈጠሩ ወንጀሎችን እና ጥፋቶችን ለመቆጣጠር እና ለማስቀረት ነው። እንደተለመደው ዘንድሮም ከዲሴምበር 23 እስከ ጀነዋሪ 6 ቀን 2017 ድረስ በከተማዎች አደባባይ (ከቤት ውጪ) የአልኮል መጠጦች እንዳይጠጡ የሚከለክለው እገዳ ተግባራዊ ተደርጓል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ታዲያ አንድ ለየት ያለ ክስተት መፈጠሩን የዓለም መገናኛ ብዙሃን ሊቀባበሉት ሰንብተዋል።


ነገሩ እንዲህ ነው። በእነዚህ ቀናት ውስጥ አልኮል ሳይጠጡ መቆየት ያልፈለጉ ይሁኑ በስራቸው ለየት ብለው መታየት የፈለጉ ሰዎች ባይታወቅም፤ የሰባት ሰዎች ስብስብ የሆነ አንድ ቡድን ይሄንን ጊዜ በተለየ መልኩ በመጠጥ አሳልፎታል። ሰባት አባላትን የያዘው ይህ ቡድን በግዛቲቱ በሚገኘው ታይራዋ ወንዝ ላይ የራሱን ደሴት በመፍጠር የፈለገውን የአልኮል መጠጥ ሲጎነጭ ሰንብቷል ሲል ኒውዚላንድ ሄራልድ የተባለው የሀገሪቱ የዜና አውታር አስነብቧል። የቡድን አባላቱ በወንዙ መካከል ላይ በርካታ ጭቃ በመሰብሰብ ብዙ ሰዎችን ሊይዝ የሚችል መደብ አዘጋጅተዋል። በዚህ በወንዙ እምርት ላይ በተሰራው መደብ ላይ አግዳሚ ወንበሮችን በመደርደር የሚፈልጉትን የአልኮል መጠጥ አይነት ያለማንም ከልካይነት ሲያንደቀድቁት ሰንብተዋል።


የቡድኑ አባላት ያመጡት የፈጠራ ስራ እጅግ አስደናቂ መሆኑን የደገፈው የግዛቲቱ ፖሊስ፣ እነዚህ አባላት የወጣውን ህግ ሳይጋፉ የራሳቸውን አለም ፈጥረው ጊዜያቸውን የማሳለፋቸውም ደግፏቸዋል። የቡድኑ አባላት ባመጡት አዲስ ሃሳብ እየተዝናኑ ህጉንም እያከበሩ በዚህ መልኩ በማሳለፋቸው የሀገሪቱ ፖሊስ አድናቆቱን ሲለግሳቸው አለም ደግሞ ልምዳቸውን ሲቀስም ሰንብቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
105 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 843 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us