የአለማችን ውዱ የገና ዛፍ

Wednesday, 03 January 2018 17:00

 

ምንም እንኳን የክርስቶስ ልደትን አስመልክቶ ቤትን በተለያዩ ዘመናዊ ጌጣጌጦችና ሰው ሰራሽ ዛፍ ማስዋብ የፈረንጆቹ ባህል ቢሆንም በእኛ ሀገርም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገር በቀል ልማድ ወደመሆኑ እየተቃረበ ነው። ያለንበት ወቅት ሰሞነ ገና በመሆኑ እኛም ለዛሬው የዓለማችን እጅግ ውድ የሆነውን የገና ዛፍ እናስተዋውቃችሁ።


በአለማችን ላይ በዋጋው ተወዳዳሪ ያልተገኘለት የገና ዛፍ መገኛው ቅንጡው የአቡ ዳቢ ሆቴል ነው። ኤምሬትስ ፖላስ የሚባለው ይህ ሆቴል 13 ሜትር ርዝመት ያለው ሰው ሰራሽ አረንጓዴ የገና ዛፍ ባለቤት ነው። የገና ዛፉ በተለያዩ ከወርቅ እና ከብር በተሰሩ ተንጠልጣይ ኳሶች እና መብራቶች ያሸበረቀ ሲሆን፣ በርካታ ከእንቁዎች የተሰሩ የአንገት ሀብሎች፣ የጆሮ ጌጦች እና ከዳይመንዶች እና ከተለያዩ የከበሩ እና ውድ ከሆኑ ድንጋዮች በተሰሩ ጌጣጌጦች አሸብርቋል። ይህ የገና ዛፍ አጠቃይ ዋጋው 151 ሚሊዮን የሳውዲ ሪያል (900 ሚሊዮን ብር ገደማ) ነው። የገና ዛፉ ይሄን ያህል ዋጋ እንዲኖረው ያደረገውም በላዩ ላይ የተደረጉት ጌጣጌጦች ዋጋ ውድነት መሆኑ ተገልጿል። በዚህ የገና ዛፍ ላይ ከተቀመጡት ውድ እንቁዎች መካከልም 181 ዳይመንዶች ይገኙበታል። ከዚህ ውጭ ግን ዛፉ ብቻውን 137ሺህ የሳውዲ ሪያል ዋጋ እንዳለው ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም በዛፉ ላይ የተደረጉት ጌጣጌጦች ዛፉን እጅግ ውብ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ የአለማችን ውዱ ዛፍ አስብለውታል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
127 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 891 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us