ዶሮዎች የፖስታ እደላን እያስተጓጎሉ ነው

Friday, 12 January 2018 17:08

በአሜሪካ አሃዩ ግዛት የሚኖሩ በርካታ ሰዎች በየዕለቱ ማግኘት ያለባቸውን የፖስታ አገልግሎት እያገኙ እንዳልሆነ እየተናገሩ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ዶሮዎች መንገድ እየዘጉ እና በፖለስታ አዳዮች ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸውን ነው። በሮኪ ሪቫር ግዛት ቅርንጫፍ ፖለስታ አገልግሎት እንደገለፀው፤ በግዛቲቱ በርካታ ዶሮዎች ምግብ ለመመገብ ወደ አንድ ስፍራ በማምራት መንገድ እየዘጉ የፖሊስ እደላውን እያስተጓጎሉ ነው። በአቅራቢው በርካታ ሰዎች ዶሮዎችን እና አዋፋትን በመመገብ የሚዝናኑ መሆናቸውን ተከትሎ በርካታ ደሮዎች ግዛቲቱን እያጥለቀለቋት መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ይሄንን ድርጊት የሚፈፅሙ ሰዎች ከዚህ ደርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተጠይቀዋል።

 

ዶሮዎቹ በብዛት ተከታትለው የሚጓዙ በመሆናቸው መንገድ ከመዝጋታቸውም በተጨማሪ በፖስታ አዳዮች ላይ የንክሻ ጉዳትም እያደረሱ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፤ በዚህ ድርጊታቸውም ከ25 እስከ 30 የሚሆኑ ቤቶች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ፖስታ ማግኘት እንዳልቻሉ ፖለስታ አገልግሎቱ ገልጿል። እነዚህ ዶሮዎች ምንም እንኳን የከፋ ባይሆንም በፖስታ አዳዮች ላይ በተለያየ ጊዜ የንክሻ ጉዳት በማድረሳቸው በስራቸው ላይ ከፍተኛ ችግር እየተፈጠረ መሆኑን የገለፀው ፖስታ አገልግሎቱ የግዛቲቱ ነዋሪዎች ዶሮዎቻቸውን በመቆጣጠር እንዲሁም ዶሮ የሚመግቡ ሰዎች ከድርጊታቸው በመቆጠብ እንዲተባበሩት ጠይቋል ሲል ያስነበበው ዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርናሽናል ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
85 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 949 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us