ከ60 ዓመት በኋላ የታወቀው ወንድማማችነት

Friday, 12 January 2018 17:09

 

አቶ ዋልተር ማክፈርሌን እና አላን ሮቢንሰን ከ60 ዓመት በላይ በጥብቅ ወዳጅነት ኖረዋል። እነዚህ ሰዎች ገና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሳሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝነተዋል። አንድ ተማሪ በትምህርት ቤት በጋራ ሊያደርጋቸው የሚችለውን ነገሮች ሁሉ በጋራ አድርገዋል። እግር ኳስ መጫወት፣ መላፋት እንዲሁም መቃለድ እና መሰል ድርጊቶችን በጋራ ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ወደ ጉርምስናው ሲቃረቡም ተመሳሳይ ሴት ማግባት እንደሚፈልጉ ሲያወሩ እንደነበር፤ የእረፍት ጊዜያቸውንም በጋራ እንደሚያሳልፉ ተገልጿል። ትዳር መስርተው ልጆች ከወለዱ በኋላም ቤተሰባቸው በጋራ በርካታ ነገሮችን ሲያከናውኑ ቆይተዋል።


ሁለቱ ሰዎች በዚህ መልኩ ከወንድማማችነት ባላነሰ ቅርበት በጋራ በሚኖሩበት ወቅት ታዲያ አንድ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ። ዋልተር በአካል የማያውቃቸውን አባቱን ፍለጋ የዘረመል (DNA) ምርመራ ማድረግ ይጀምራል። በዚህ አጋጣሚ ሮቢንሰን ጓደኛቸው ብቻ ሳይሆኑ እውነተኛ ወንድማቸው መሆናቸውን ተረዱ። ነገሩ እጅግ ግርምትን የፈጠረባቸው እንደነበረ ሁለቱም ተናግረዋል። አሁን ዋልተር እና ሮሲንሰን ከልብ የሚዋደዱ ጓደኛሞች ብቻ ሳይሆኑ ከአንድ እናት እና አባት የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ዋልተር በ1943 እንዲሁም ሮቢንሰን በ1945 በሆኖሉሉ ከተማ ነበር የተወለዱት። በውል ባልታወቀ ምክንያትም የእነ ዋልተር እናት ሮቢንሰንን በሀዋይ ለሚገኙ ሰዎች በጉዲፈቻ መልክ ይሰጡታል። በወቅቱ ጉዲፈቻው የተደረገው በባህላዊ መልክ ስለነበረ ምንም አይነት መደበኛ ማስረጃ ማግኘት አልተቻለም ነበር። ሮቢንሰንም ስለ ወላጅ አባቱ እና እናቱ የሚያውቀው ነገር አልነበረም። አሳዳጊ ቤተሰቦቹ እና ወላጅ እናቱ ጥሩ ጓደኛሞች እንደሆኑ ግን ተናግሯል። “የዋልተር እናት እና እናቴ ጥሩ ጓደኛሞች ነበሩ። እናቴ የትምህርት ቤት ነርስ ነበረች፤ ስለዚህ ዋልተር ሊታመም ወይም ጉዳት ሲደርስበት እርዳታ የምታደርግለት እናቴ ነበረች” ሲል ወደ ኋላ ተመልሶ ተናግሯል። ከልጅነታቸው ጀምሮ ዋልተርን አጎቴ እያለ ይጠራው እንደነበረም ተናግሯል። ሳይተዋወቁ ከ60 ዓመታት በላይ አብረው የኖሩት ወንድማማች ሆነው ተገኙ ሲል ሲኤን ኤን ዘግቧል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
90 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 922 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us