“አንተን አወጣ ብዬ እኔ ልግባ!”

Wednesday, 17 January 2018 13:32

 

አንድ ፊታውራሪ ዳኛ ነበሩ። ግዙፍም ነበሩ። አንድ ጊዜ እንኳ በጋሪ ሲሄዱ የጋሪውን እንጨቶች ሰባብረው ፍርድ ቤት ተከሰው ቆመው ነበር። “ምድረ ኮረኮር እምቧጮ ውጋግራ በፈረስ እየጎተተ ቢሰበር እኔ ኪሳራ መግባት አይገባኝም። ይልቅ ከመንገድ ላይ ወድቄ እንድላላጥ ስላደረገ ባለፈረሱ ካሣ ይከፍለኛል” ብለው ተከራክረው ነበር።

ታዲያ አንድ ጊዜ ከመሸታ ቤት በተነሳ አምባጓሮ ሰበብ አንድ ሰው ሞትና ገዳይ ተይዞ ምርመራው ተጣርቶ ጉዳዩ ፊታውራሪ ዘንድ ይቀርባል። አባተ ጉቦ አይተው አይዘሉም ነበርና የገዳይ ወገኖች ሞቅ ያለ ገንዘብ ይሰጣሉ። “ግድ የለም፣ ማስረጃው በቂ አይደለም ብዬ ገዳይን አወጣዋለሁ” ብለው ቃል ገብተው ነበር። በኋላ ግን ሟችም በወቅቱ የባለሥልጣን ወገን ኖሮ “በገዳዩ ላይ ከባድ ቅጣት ካልወሰንህ ለሕይወትህም ሆነ ለጡረታህ ያሰጋሃል” የሚል ማስጠንቀቂያ ወረዶባቸው “አወጣዋለሁ” ያሉትን ሐሳብ ሰርዘዋል።

የፍርድ ቀን ቀረበ። ዓቃቤ ሕግና የተከላካይ ጠበቃ የመፋረጃ ሐሳብ ሰጡ። ፊታውራሪው በወጉ አስተካክለው ገዳይን ዕድሜ ልክ እስራት ፈረዱበት።

ወንጀለኛውም “ፊታውራሪ አወጣሃለሁ ብለው የገቡትን ቃል አጠፋብኝ። የልጆቼ ማሳደጊያ የሚሆነውን ገንዘብ ሰጥቼ መና ቀረሁ” አለ ወንጀለኛ።

“እኝኝዋ” አሉ ፊታውራሪ በማፌዝ። “አንተን አወጣለሁ ብዬ እኔ ገብቼ ልቀርልህ ነው!”

                           ሙሻዘር - በመርስኤ ሀዘን አበበ 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
102 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 939 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us