የ6 ቀናት ትውውቅ ጋብቻ

Wednesday, 17 January 2018 13:33

 

ከዚሁ ከትዳር ጉዳይ ሳንወጣ የስድስት ቀኑን ጋብቻ ጉዳይ እናንሳ። ይሄ ጋብቻ ስድስት ቀናትን የፈጀ ጋብቻ ሳይሆን በስድስት ቀናት ትውውቅ የተመሰረተ ጋብቻ ነው። ነገርየው የተከናወነው በናይጄሪያ ነው። የፈረንጆቹ 2017 መጠናቀቂያ በሆነው ዲሴምበር 30 የተወጠነው ጋብቻ ከስድስት ቀናት በኋላ ድል ባለ ሰርግ ተጠናቋል ሲል ያስነበበው ቢቢሲ የዜና አውታር ነው።

ናይጄሪያዊው ቺዲማ አሜዱ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ጋብቻ መመስረት እንደሚፈልግ፣ ጋብቻውን ከእርሱ ጋር መመስረት የምትፈልግ ሴት ካለችም እንድትገናኘው የሚገልፅ ማስታወቂያ ይለቃል። “እድሜዬ እየገፋ ነው። አሁን ምንም ጊዜ ሳላጠፋ ትዳር መመስረት እፈልጋለሁ። ጋብቻዬንም ጃንዋሪ 6 ቀን 2018 ማድረግ ፈልጋለሁ። ለትዳር የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን አሟላለሁ የምትይ ሴት ማመልከቻሽን መላክ ትችያለሽ። ማመልከቻ የማስገቢያው የመጨረሻ ቀን ነገ እኩለ ሌሊት ነው።” የሚል መልዕክቱን በፌስቡክ ገፁ ላይ ያሰፈረው አሜዱ፣ ማስታወቂያውን ከለቀቀ በኋላ የአመልካቾችን ምላሽ መከታተል ጀመረ። መልዕክቱን የተመለከቱ በርካታ ሴቶችም ማመልከቻቸውን አስገቡ። ከእነዚህ ሴቶች መካከል ግን ቀልቡን የሳበው ሶፊ የተባለችው ሴት ማመልከቻ ነበር። ማመልከቻውን ከተመለከተ በኋላም ቀጥታ መልእክት ላከላት፤ በመቀጠልም ስልክ ደውሎ ካወሩ በኋላ መገናኘት ችለዋል። አሜዱ ከስልክ ንግግሩ በኋላ ከአቡጃ በ500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘዋ ኢኑጉ ከተማ በመጓዝ ሶፊን አግኝቷታል።

ሶፊም እርሷ ወደምትኖርበት ከተማ በሄደበት ወቅት ጥሩ አቀባበል አድርጋለታለች። መጀመሪያ ላይ ቀልድ መስሏት እንደነበረ የገለፀችው ሶፊ፣ ስትመለከተው ግን እጅግ ቆንጆ፣ ሳቢ እና ማራኪ ወንድ ቢሆንም የትዳሩን ጉዳይ ግን በቁም ነገር አሳብቦታል በማለት ተቸግራ እንደነበር ተናግራለች። በመቀጠልም አሜዱ ሶፊን ይዟት ወደ አጎቱ ቤት በማምራት የሚያገባት ሴት እርሷ መሆኗን ሲናገር ስትሰማ ነገሩ እውን ወደመሆኑ እየተቃረበ በመሆኑ መደሰቷን ገልፃለች። ሶፊ እና አሜዱ ለረጅም ዓመታት የፌስ ቡክ ጓደኛሞች እንደነበሩ የገለፀችው ሶፊ፣ ነገር ግን አንድ ቀን እንኳን ተፃፅፈው እንደማያውቁ ተናግራለች። በዚህ መልኩ ለስድስት ቀናት የቆየው ትውውቅ ወደ ትዳር አምርቶ ባለፈው ዳንዋሪ 6 ቀን 2018 ኢግቦ በተባለው ባህላዊ የሰርግ ስነሥርዓት ተደምድሟል። በመጪው ሚያዝያም በቤተክርስቲያን ስነሥርዓት ጋብቻቸውን እንደሚያስሩ ተናግረዋል። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
113 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1137 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us