በበረዶ ላይ የተቀረፀው የጋብቻ ጥያቄ

Wednesday, 17 January 2018 13:33

 

ሰዎች የወደፊት የትዳር አጋራቸው እና የህይወት ውሃ አጣጫቸውን ለማግኘት የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም። በተለይ ልባቸው የፈቀደው እና ከልብ ያፈቀሩትን ሰው ለራሳቸው ለማድረግም በህይወት ዘመን የማይረሱ ድንቅ ፈጠራዎችን ለማሳየት ሲጣጣሩ ይታያሉ። የዚህ ፈጠራ አካል የሆነ አንድ ዜናም ከወደ አሜሪካ ሰሞኑን ተሰምቷል። ነገሩ እንዲህ ነው፤ የሰሜን ዳኮታ ዩኒቨርስቲ አውሮፕላን በረራ ትምህርት ቤት ተማሪው ጋቪን ቤከር ፍቅረኛውን ለጋብቻ ለመጠየቅ ሲል በበረዶ ግግር ላይ መልዕክቱን አስፍሯል። ኦሊቪያ ቶፍት ለተባለችው ፍቅረኛው ታገቢኛለሽ ወይ? የሚለውን ጥያቄ ለማቅረብ በበረዶ ግግር ላይ እጅግ ግዙፍ የሆነ የልብ ቅርፅን ቀርፆ እንዲሁም መልዕክቱን ጽፎ ታይቷል። ኢን ዊ ጎ በተባለው ሪዘርት በሚገኘው የበረዶ ግግር ላይ መልዕክቱን በዚያ መልኩ ቅዝቃዜውን ተቋቁሞ እና የራሱን ፈጠራ አክሎበት የጋብቻ ጥያቄ ማቅረቡን ብዙዎች በአድናቆት የተቀባበሉት ሲሆን፤ ፍቅረኛውም በታላቅ መገረም ውስጥ ሆና ጥያቄውን ያለ ምንም ማንገራገር ተቀብላዋለች ሲል ያስነበበው ዩፒ አይ ድረ -ገፅ ነው። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
113 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 987 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us