ይህን ያውቁ ኖሯል?

Wednesday, 24 January 2018 14:17

 

- የሰው ልጅ አፍንጫ 50ሺህ ያህል መዓዛዎችን ማስታወስ ይችላል።
- በማርስ ላይ ፀሐይ በምትጠልቅበት ወቅት የሚታየው ቀለም ሰማያዊ ነው።
- በእንቅልፍ ውስት ሆነን እንኳን ጆሯችን መስማት አያቆምም።
- የጆሮ ኩክ ከዘይት፣ ከላብ እና ከሞቱ ሴሎች የተሰራ ሲሆን ጆሮን የማጽዳት አገልግሎትም አለው።
- በምድራችን ላይ ካለው የሰው ልጅ ቁጥር ይልቅ በአንድ ሰው ቆዳ ላይ የሚኖሩ ህይወት ያላቸው ነገሮች ቁጥር ይበልጣል።
- አንዲት ጥቅል ዳመና ከ1 ሚሊዮን ቶን በላይ ክብደት አላት።
- የአለማችን እድሜ ጠገቡ ማስቲካ ከ9ሺህ ዓመት በላይ እድሜ አለው።
- በሞንጎልያ ህጻናት የወተት ጥርሳቸውን ሲነቅሉ ጥርሱ በስብ ወይም በስጋ ተጠቅልሎ ውሻ እንዲበላው ይደረጋል።
- በካናዳ ኦንታዮሪ የድምፅ ብክለትን ለመቀነስ ሺባል ዝም ብሎ ማፏጨት፣ መዝፈን እና መጮህ የተከለከለ ነው።
- በፊጂ ጋብቻ መፈፀም የፈለገ አንድ ጉብል ለወደፊት ወንድ አማቱ የአሳ ነባሪ ጥርስን በስጦታ መልክ ማምጣት ይኖርበታል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
131 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us