በጠርሙስ ስብርባሪ ላይ እስከመጓዝ የተከፈለ መስዋዕትነት

Wednesday, 31 January 2018 12:56


የቨርጂኒያው ነዋሪ የህፃናትን ህይወት ለመታደግ ካለው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ የደረሰበት ደረጃ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ አሰኝቶታል። ራዜል ካሴቫህ የተባለው የቨርጂኒያ ነዋሪ በግዛቲቱ የህፃናትን ህይወት ለመታደግ የሚያገለግል ሆስፒታል ለማስገንባት የድርሻውን ለመወጣት ብዙ ነገሮችን ሲያወጣና ሲያወርድ ቆይቷል። በመጨረሻም በተሰባበሩ ጠርሙሶች ላይ በባዶ እግሩ በመጓዝ የተወሰነ ገቢን ለማሰባሰብ ወሰነ። በውሳኔው መሠረትም ባለፈው ሳምንት በርካታ ሰዎች በተሰበሰቡበት የጠርሙስ ስብርባሪዎች ተነጥፈውበት በተዘጋጀለት ቦታ ላይ ጫማውን አውልቆ ከባዶ እግሩ ጉዞ ጀመረ። ጥርሱን ነክሶም የቻለውን ያህል ለመጓዝ ሞከረ። በመጨረሻም 120 ጫማ ርዝመት ያለውን መንገድ በተጎዘጎዘለት የጠርሙስ ስብርባሪ ላይ በመጓዝ አለምን አስደመመ። ይሄንን ጥንካሬውን ያየው የአለም ድንቃ ድንቅ መዝገብም ይሄን ያህል ርቀት በዚህ አይነት መንገድ ላይ የተጓዘ የለም ብሎ ከክብረወሰኑ አስጨብጦታል።


ካሴቫህ ባደረገው የባዶ እግር የጠርሙስ ላይ ጉዞ 200 ፓውንድ ክብደት ያለው የጠርሙስ ስብርባሪ እንደተነጠፈለትም ተገልጿል። እያንዳንዱን እርምጃ ሲራመድ በጠርሙስ ስብርባሪዎቹ ላይ እየቆመ እንዲሁም እርምጃውን ሳያቋርጥ እንደሆነም በተቀረፀው ቪዲዮ ተመልክቷል። የእግር ጉዞውን ካጠናቀቀ በኋላ ለጉዞው አበረታች መድሐኒት መጠቀም አለመጠቀሙን እንዲሁም ማለስለሻዎችን ለእግሩ መጠቀም አለመጠቀሙን ለማረጋገጥ ዶክተሮች ምርምሩ ያደረጉለት መሆኑን የዘገበው ቢቢሲ የዜና አውታር ነው። ክብረ ወሰኑን ከያዘ በኋላም በውስጥ እግሩ ላይ የደረሰበትን የመሰነጣጠቅ እና የመቆራረጥ ጉዳት በአፋጣኝ መታከም እንዳለበት ተነግሮታል። ይህ በጠርሙስ ስብርባሪ ላይ የሚደረግ የባዶ እግር ጉዞ ክብረ ወሰን ቀደም ሲል 85 ጫማ ርዝመት በተጓዘ ሰው ተይዞ እንደነበረ ያስነበበው ዘገባው፤ ካቤቫህ ከክብረ ወሰኑ በተጨማሪም ያለውን መልካምነት ያሳየበት ተግባር ተብሎ አድናቆትን አትርፎለታል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
96 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 539 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us