እውን የሆነው የህልም ሎተሪ

Wednesday, 07 February 2018 13:11

የቨርጂኒያ ነዋሪው ቪክቶር ኤምሊ ሰሞኑን የ400 ሺህ ዶላር ሎተሪ አሸናፊ ሆኗል። የሎተሪ አሸናፊነት የተለመደ በመሆኑ ሊያስገርመን አይችል ይሆናል። ነገር ግን የኤምሊ አሸናፊነት ለየት ያለ ነበር። ኤምሊ ሌሊት እንቅልፍ ወስዶት ሳለ 3፣10፣17፣26 እና 32 ቁጥሮችን በህልሙ ያያል። ከእንቅልፉ ሲነቃም ስለቁጥሮቹ ማሰላሰሉን አላቆመም። በዚህን ጊዜም ለምን በእነዚህ ቁጥሮች ሎተሪ አልቆርጥም ሲል ከራሱ ጋር ተማከረ፤ እናም አደረገው። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ህልም በፍፁም አይቶ እንደማያውቅ የተናገረው ኤምሊ፤ በህልሙ ያያቸው ቁጥሮች ያሏቸው አራት የሎተሪ ትኬቶችን ገዛ። የሎተሪ እጣው ሲወጣም በአራቱም የሎተሪ ትኬቶች ኤምሊ አሸናፊ ሆነ። እያንዳንዳቸው የአንድ መቶ ሺህ ዶላር ሽልማት ያላቸውን የሎተሪ ትኬቶች በማሸነፍ በድምሩ የ400ሺህ ዶላር ባለቤትም ለመሆን በቃ። ህልም እንደፈቺው ነው ቢባልም ህልሙን በዚህ መልኩ የተረጎመው ኤምሊ ያላሰበውን ሲሳይ ማግኘት ችሏል። ይግረማችሁ ሲል ዜናውን ያሰራጨው ዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርናሽናል ነው።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
86 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us