በውስኪ የተገነባ ጥንካሬ

Wednesday, 07 February 2018 13:13

 

ጃክ አካ የ105 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸው። አብዛኞቹ አረጋውያን እጅ ሰጥተው በሌሎች እጅ ላይ በሚወድቁበት በዚህ እድሜ ላይ ሆነው አረጋዊው ጃክ ከወጣት ያልተናነሰ ተግባርን እያከናወኑ ይገኛሉ። ከዚህ ቀደም በርካታ አስደናቂ ነገሮችን በማከናወን ስማቸውን በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ በተደጋጋሚ ያስፈሩት አቶ ጃክ፤ ባለፈው ዓመትም ከባድ የግንባታ ተሽከርካሪን በማሽከርከር ባለረጅም እድሜው በመባል ስማቸውን በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ አስፍረዋል። በተጨማሪም በዚያው ዓመት የ104 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ሆነው ሳለ ግዙፍ ጀልባን በማሽከርከር በዚህ እድሜ ላይ ሆነው ጀልባን በማሽከርከር ክብረ ወሰኑን ጨብጠዋል። በ102 ዓመታትም የበረዶ ላይ ሸርተቴን በማድረግ ተወዳዳሪ አልተገኘላቸውም።


ከላይ የተዘረዘሩትን በርካታ አስደናቂ ተግባራት ያከናወኑት የእድሜ ባለፀጋው ጃክ ታዲያ ለዚህ ዓይነቱ ጥንካሬያቸው ምስጢር የሆነውን ነገር ሰሞኑን ወደ ሚዲያው ብቅ በማለት ተናግረዋል። ለቢቢሲ እንደገለፁትም “ሁልጊዜ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ንፁህ አየር ማግኘት እና በሚወዱኝ ቤተሰቦቼ የዚህ ሁሉ ተግባራት ውጤት ናቸው። ከሁሉም በላይ ግን ጥንካሬዬ የተገነባው በውስኪ ነው” ብለዋል። ከአራቱ ልጆቻቸው የመጨረሻዋ የሆነችው የ57 ዓመቷ ጆኒ ጉድዊን እንደገለፀችውም አባቷ ማለዳ ላይ ሻይ በውስኪ የሚጠጡ ሲሆን ማታ ላይ ደግሞ ሁለት መለኪያ ውስኪ ከሎሚ ጭማቂ ጋር ጠጥተው ወደ መኝታቸው እንደሚሄዱ ገልፃለች። ከራሳቸው አልፈውም ልጆቻቸው እንደ ጉንፋን ያሉ ችግሮች ሲገጥሟቸው ውስኪን እንደመድሐኒት እንደሚያዙላቸው ልጃቸው ተናግራለች። ከዚህ በተጨማሪ ግን ሰዓታቸውን ጠብቀው በቀን ሶስት ጊዜ ብቻ ምግብ እንደሚመገቡ ተናግረዋል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
118 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 434 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us