የእናት ቅናት

Wednesday, 14 February 2018 11:51

 

አንዲት እናት በልጇ ላይ ምን ያህል ልትቀና ትችላለች? ከሰሞኑ ማትሮ የዜና አውታር ያስነበበው ዜና ሁላችንም ይሄንን ጥያቄ መላልሰን እንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው። የ44 አመቷ እናት በ11 አመት ልጇ ላይ ያላት ቅናት ከማንም ከምንም አይገጥምም ይላል ዜናው። ኤ ጂ የተባለችው ይህች እናት የአብራኳ ክፋይ የሆነው ልጇ ተፈጥሮ ከቸረችው ውበት ውስጥ አንዱ በጉንጩ ላይ ያለችው ስርጉድ (ዲምፕል) ናት። እናት ታዲያ በልጇ ውበት ከመደነቅ እና ከመደሰት ይልቅ ከባድ የቅናት መንፈስ ያሳድርባታል። እናም ራሷን ከልጇ እኩል ለማድረግ አንድ ለየት ያለ ተግባርን ፈፀመች።


ኤጂ ወደ ቀዶ ህክምና ሆስፒታል በማምራት ልክ እንደልጇ አይነት ስርጉድ በፊቴ ላይ እንዲኖረኝ ስለምፈልግ ይሰራልኝ ስትል ባለሞያዎችን ጠየቀች። ባለሞያዎቹም መስራቱን እንሰራለን ነገር ግን ቀዶ ህክምናውን ተከትሎ ለሚመጣው ነገር ኃላፊነቱን አንወስድም ሲሉ ያለውን ነገር ለማስረዳት ሞክረዋል። አሻፈረኝ ያለችው እናትም ለቀዶ ህክምናው የ1ሺህ 300 ዩሮ ገንዘብን ወጪ በማድረግ ቀዶ ህክምና አድርጋለች። ቀዶ ህክምናው ከጉንጯ ላይ በመቁረጥ እና መልሶ በመስፋት የተደረገላት ሲሆን፤ ለቀዶ ህክምናውም አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የፈጀ ጊዜ ወስዶባታል። ከህክምናው በኋላ በሴትየዋ ጉንጭ ላይ እብጠት እና ጎልቶ የሚታይ ጠባሳ የቀረ ሰሆን፣ እርሷ የፈለገችው አይነት ስርጉድ እስካሁን ድረስ አልተፈጠረም። እርሷ ግን እያደር የፈለገችው አይነት ዲምፕል እንደሚፈጠር በታላቅ ተስፋ እየተጠባበቀች ትገኛለች።


“አንዳንድ ሰዎች በተሰጠውን ነገር መደሰት አለብን ብለው ስለሚያስቡ የእኔን ድርጊት እንደ ቅንጦት ወይም እንደ እብደት ሊቆጥሩት ይችላሉ። ነገር ግን የልጄን ዲምፕል ካየሁ በኋላ እንዲህ አይነት ዲምፕል እንዲኖረኝ ፈለኩኝ። ይሄንን ነገር ለመወሰን ከአስር ዓመት በላይ ሳስብበት እና አማራጮችን ስፈልግ ነው የኖርኩት። ይሄን ሳደርግ ቀዶ ህክምናው የሚደረገው በጉንጬ ላይ በመሆኑ ተያያዥ ብዙ ችግሮች እንደሚኖሩ አውቃለሁ። ነገር ግን ቤተሰቦቼን ለገንዘብ ችግር እስካልዳረኳቸው ድረስ ይሄን ገንዘብ ከፍዬ በማድረጌ ምንም አይነት የጥፋተኝነት ስሜት አይሰማኝም ስትልም አስረድታለች።

 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
147 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1086 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us