መረገጥ የሚገባው ምላስ!

Wednesday, 14 February 2018 11:38

 

የሐሜት ቃል /አሉባልታ ተናጋሪ ነው የተባለ የአንድ ሥራ ዘርፍ ኃላፊ ነበር። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖትን ምሕረት ለማግኘት የሚቻለውን ሁሉ አድርጎ የማይፈፀምለት ሲሆን፣ ከቅርብ አገልጋያቸው ጋር ሲነጋገር “በሩን ከፈት አድርገህልኝ፣ እጫማቸው ላይ ወድቄ ምህረት እንድለምናቸው ብቻ ፍቀድልኝ” አለው። በትረያሬኩ ቢሮዋቸው ገብተው እንደተቀመጡ በሩን ሲከፍትለት ፈጠን ብሎ ይገባና ጫማቸውን ከሳመ በኋላ። እግራቸውን አንስቶ እጀርባው ላይ ያደርግና “ቅዱስ አባታችን እንግዲህ ደህና አድርገው የፈለጉትን ያህል ይርገጡኝ። ምህረት ሳያደርጉልኝ ከጫማዎት ስር አልነሳም” አላቸው። እርሳቸውም እም- እም “ጀርባህን ሳይሆን መርገጥ የሚገባኝማ ምላስህን ነበር” ማለታቸው ይታወሳል።


ሌላም ጊዜ ደግሞ ከአንድ ሊቀ ጳጳስ ጋር አለመግባባት ተፈጥሮባቸው አዝነው በነበሩበት ወቅት፣ ወደ ደብረ ዘይት ለመሄድ በማርቸዲስ ሲጓዙ አንድ የገበሬ ኮርማ አስፋልት መንገድ ላይ ቆሞ ፊው፣ እምቧ እያለ አላሳልፍ ሲላቸው “ዘወር በል እባህክ! ይኸ ደግሞ እንደ አባ እከሌ ጫንቃውን አሳብጦ ምን ይጎማለልብናል?” አሉ። በቀይ ሽብር ወቅትም “በውጪው ዓለም የሰው ሕይወት ማጥፋት ይቅርና ዛፍ እንኳ እንዳይቆረጥ ጥንቃቄ ይደረግለታል። ታዲያ በሀገራችን የሰው ዘር ሕይወት ላይ ይህን ያህሉን ከገደብ ያለፈ ጭካኔ ምን አመጣው?” ሲሉ የተናገሩበት ጊዜም እንደነበር ይታወሳል።
ልዩ የአርበኝነት ባህርይ ሲደመር ወታደራዊ ክሂል - በመጋቤ አእላፍ መክብብ አጥናፍው

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
86 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us