እንዲህም አለ

Wednesday, 21 February 2018 11:47

 

የትራንስ አቪያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን የዕለት ሥራውን በማከናወን ላይ ሳለ ያልተጠበቀ ነገር ከሥራው አስተጓጉሎታል ይላል የሰሞኑ የሜትሮ ዘገባ። በዚህ አውሮፕላን ውስጥ ከተሳፈሩ ተጓዦች መካከል አንዱ አሳፋሪ ብቻም ሳይሆን ተግባሩን የሚያስተጓጉል ተግባር ፈፀመ። ሰውዬው በተቀመጠበት ሆኖ ያስጨነቀውን አየር ማስወጣት (ፈሱን መፍሳት) ጀመረ። በስህተት አሊያም ተጨንቆ ያደረገው የመሰላቸው አጠገቡ የተቀመጡት ተጓዦች ሊታገሱት ሞከሩ። ነገር ግን ሰውዬው ከድርጊቱ ከመቆጠብ ይልቅ ለአብዛኞቹ ሊሰማ በሚችል መልኩ ይደጋግመው ጀመር።

በሁኔታው የተበሳጩት አጠገቡ የተቀመጡት ተጓዦችም ሰውዬውን ለመቅጣት በሚመስል መልኩ ለጠብ ተጋበዙ። የሰዎቹን አዝማሚያ የተመለከተው የአውሮፕላኑ አብራሪ ሰውዬው ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ተደፍረናል ያሉትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም፤ አሻፈረኝ አሉት። በመሆኑም ከዱባይ ወደ አምስተርዳም ይደረግ የነበረውን በረራ በመተው በቬና አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገዷል። ጥቆማው የደረሰው ፖሊስም ያልተገባ ድርጊት የፈፀመው ግለሰብ በተቀመጠበት ተርታ ተቀምጠው የነበሩ ሰዎችን ጭምር በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል። ሰውዬው ምን ነክቶት እንዲህ እንዳደረገ ግን የተገለፀ ነገር የለም።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
97 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1081 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us