የአንበሳና የከርከሮ ጠብ

Wednesday, 28 February 2018 12:42

 

በአንድ አካባቢ የሚኖሩ አንበሳና ከርከሮ ነበሩ። ሁለቱም የዱር እንስሳት የተፈሩና ኃይለኞች ነበሩ። አንዱ ሌላውን እንዳይነካውም ይጠነቀቁ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ሁለቱም ውሃ ለመጠጣት ወደ ወንዝ ምንጭ መጡ። ሆኖም የምንጩን ውሃ ትንሽ ስለሆነ ለመጠጣት የሚቻለው አንደ በአንድ ነበርና እኔ ልቅደም፣ እኔ ልቅደም በሚል ራስን ከፍ የማድረግ ፍላጎት ምክንያት ተጣሉ።


ጠባቸውም ወደር ወደ ሌለው ድብድብ ተቀየረ። አንዱ ሌላውን ያለ ርህራሔ ይነክሰው፣ ይቧጭረው፣ ይመታው ጀመር። ሁለቱም ትንፋሽ እስኪያጥራቸው ድረስ ሲደባደቡም ጥንብ አንሳዎችና እነሱን የመሳሰሉ ሥጋ በል አእዋፍ “አንዳቸው ወይም ሁለቱም ቢሞቱ የዕለት ምግባችንን እናገኛለን” በማለት ፈቅ ብለው ተቀምጠው ነበር።


አንበሳውና ከርከሮው ትንፋሽ ለመሳብ ትንሽ አረፍ ሲሉ በአካባቢያቸው አሰፍስፈው የተቀመጡትን አእዋፍ ተመለከቱ። ይህም ትርዕይት ሲመለከቱ የፈፀሙት ስህተት እንደሆነ አወቁ። የአካባቢ ሁኔታ ሲመለከቱም ለክብር ብለው የጀመሩትን ፀብ አቆሙ።
ከነበራቸው ንዴት ተመልሰውና ጠባቸውን አቁመውም “እርስበርስ ተጋድለን የጥንብ አንሳ ምግብ ከምንሆን ወዳጆች ብንሆን የበለጠ ይጠቅመናል” አሉ።
የኤዞፕ ተረቶች - በተሸመ ብርሃኑ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
96 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 534 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us