ስብሐትና ተረት

Wednesday, 28 February 2018 12:44

 

ከዕለታት አንድ ቀን ስብሐት ለሽምግልና ተልኮ ይሄዳል። ሽምግልናው የተላከበት ልጆቹ መጋባት ፈልገው የሴቷ አባት እንዲፈቅዱ ለወግ ያህል ለመጠየቅ ነው። ለዚህ ሽምግልና ይመጥናሉ ከተባሉት ሰዎች መካከል አንዱ ስብሐት ሆኑ። ስብሐትም ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እንዲሉ ነገሩ ገብቶታል። በሽምግልና የሚጠፋው ጊዜና ጉልበትም ከወዲሁ አድክሞታል። ነገር ግን መሄድ ስላለበት ይሄዳል። ሽማግሌዎቹ ልጅቷ ቤት ደርሰው በር ተከፍቶላቸው እንደገቡ የልጅቷ አባት ይመጣሉ። ተጨባብጠው አረፍ እንዳሉም ስብሐት ተሽቀዳድሞ ይናገራል።


“የመጣነው ልጆትን አንድ የኛ ልጅ ሊያገባ ጠይቆ ነው። እዚህ ውስጥ እርሶም ሆኑ እኛ ምንም መብት የለንም። እንቢ ቢሉ እንኳን እነሱ ለመጋባት ቆርጠው ጨርሰዋል። ስለዚህ ይጋባሉ አሁን በከንቱ ከመታከት ደስ የሚለንን ሌላ ጨዋታ እየተጫወትን እንቆይ። ምን ይመስልዋል? አላቸው። የልጅቷ አባት ስብሐትን ያውቁት ኖሮ ስቀው “ጥሩ” አሉና ሌላ ጉዳይ ሲጨዋወቱ ዋሉ።


አንድ ጊዜ ደግሞ አንድ ወጣት ፀሐፊ ከስብሐት ጋር ይተዋወቅና ስሙን ከነገረው በኋላ እጅግ ቅር ተሰኝቶ “ጋሽ ስብሐት አላስታወስከኝም እንጂኮ ስንተዋወቅ ከዛሬ ጋር ሶስተኛ ጊዜያችን ነው” አለው። ስብሐትም ቀልጠፍ ብሎ “እድሜ ከሰጠን ገና ሰባ ሰባት መተዋወቅ ይቀረናል” አለው።


በሌላ ጊዜ ደግሞ ስብሐት ጫት ሲቅም የደረሰ አንድ ወጣት ነው አሉ። ይመክረዋል። “ጋሽ ስብሐት፣ አይቃሙ፣ መቃም ሱስ ያሲዛል እኔ አልቅምም” ይለዋል። ስብሐት ዝም ይልና ሲጋራ ይለኩሳል። ወጣቱ ምክሩን ይቀጥላል።

 

 

“ጋሽ ስብሐት አያጭሱ ማጨስ ሱስ ያሲዛል፤ እኔ አላጨስም” ይለዋል። ስብሐት ዝም ይልና ቡና ያዝዛል። “ትጠጣለህ?” ወጣቱን ሊጋብዝ ይጠይቀዋል። “ቡና አልጠጣም፣ ሱስ ያሲዛል” ይለዋል። ስብሐት ዝም ይለዋል።

 

 

በመጨረሻ ሁሉም አልቆ መጠጣት ሲጀምር ወጣቱ “መጠጥ ሱስ ያሲዛል አይጠጡ። እኔ ሱስ እንዳይዘኝ አልጠጣም” ይለዋል። ስብሐትም ገረፍ አድርጎ አይቶት “አላመለጥክም፤ ሱስ የመፍራት ሱስ አለብህ” አለው።
ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ህይወትና ክህሎት….. አለማየሁ ገላጋይ

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
114 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1071 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us