አስገራሚዎቹ የአፍሪካ ህጎች

Wednesday, 14 March 2018 13:02

 

እያንዳንዱ ሀገር እና ሀጉር የየራሱ የሆነ ህግና ልማዶች አሉት፡፡ ሁሉም በሚያምንበት መንገድ ህጎች የሚያወጣ ቢሆንም የአንዱ ሀገር ህግና ልማድ ለሌላው ሀገር ህዝብ አስገራሚና ለማመን የሚከብድ ሊሆን ይችላል፡፡ እስኪ እኛም በአፍሪካ ሀገራት ካሉት ህግና ደንቦች የተወሰኑትን እንጠቃቅስ፡፡

-    በኬንያ አንድ ሰው ምንም ገንዘብ በኪሱ ውስጥ ሳይኖረው በእግሩ ሲዘዋወር በተቆጣጣሪዎች ከተደረሰበት ሕገ-ወጥ ድርጊት በመሆኑ ይቀጣል፡፡

-    በጊኒ ወላጆች ለልጃቸው ሞኒካ የሚል ስም ማውጣት ህገ-ወጥነት ነው፣

-    በናይጄሪያ ህግ መሠረት ቢራ፣ የማዕድን ውሃ፣ ለስላሳ መጠጦች እና ፍራፍሬ ከውጭ ሀገራት ማስገባት ክልክል ነው፡፡

-    በናይጄሪ ጋብቻ የመፈፀሚያ ዝቅተኛ እድሜ ስላልተቀመጠ ከ12 ዓመት ጀምሮ እድሜ ያላቸው ታዳጊዎች ጋብቻ ይፈፅማሉ፡፡

-    በሞሮኮ ተገደው የተደፈሩ ሰዎች ወንጀለኞች ተብለው ይቀጣሉ፡፡ ቅጣቱን ለማምለጥ ከፍለጉ ደፋሪያቸውን እንዲያገቡ ይደረጋል፡፡

-    የኢኳቶሪያል ጊኒ ነዋሪዎች የውጭ ሀገራት መጽሀፍትን፣ ጋዜጦችን እና መጽሔቶችን እንዲያነቡ አይፈቀድላቸውም፡፡ ዜጎች በአጠቃላይም እንዲያነቡ አይመከርም፡፡

-    በኤርትራ ዜጎች እምነታቸውን ከመተግበራቸው ከፊት ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ በሀገሪቱ ህግ መሠረት እንደ ኦርቶዶክስ እምነት እና እስልምና ያሉት ዋና ዋና እምነቶች ብቻ እውቅና ያላቸው ሲሆን፤ ከእነዚህ ውጭ የሆኑትን እምነቶች በይፋ ሲያራምድ የተገኘ ነው በህግ ይጠየቃል፡፡

-    በቻድ አስቀድሞ ፈቃድ ሳያገኙ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ላይ ፎቶግራፍ ማንሳት በህግ የተከለከለ ነው፡፡

-    በግብፅ በአየር መንገድ አካባቢ አጉሊ መነፅር ሲጠቀም የተገኘ ሰው በእስራት ይቀጣል፡፡

-    በደቡብ አፍሪካ የፕሬዝዳንቱን መኖሪያ ቤት ፎቶ በየትኛውም የመገናኛ ብዙሃን ዘዴ ላይ መጠቀም ሕገ-ወጥ ድርጊት ነው፡፡

-    በሞዛምቢክ ከከተማ አስተዳደር ፈቃድ ሳያገኙ መኖሪያ ቤትን ቀለም መቀባት በህግ ያስቀጣል፡፡

-    በማላዊ በአደባባይ ላይ አየር ማስወጣት (ፈስን መፍሳት) በህግ ያስቀጣል፡፡

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
150 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 545 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us