“ተገርፎ ያደገ”

Wednesday, 25 April 2018 12:36

ሰውየው በአዋሳ ከተማ የገንዘብ ሚ/ር ባልደረባ ሆነው ይኖሩ ነበር። መቼም በ “ሞዴል” ማማታት፣ ማጭበርበርና ገንዘብ የሚገኝበት ጎዳና ሁሉ በመጥረግ የታወቁ ናቸው። የመንግሥትን ገንዘብ እንዴት አድርጎ እንደሚወሰድ የሚያውቁ አስፈላጊ ከሆነም ለሌሎች ትምህርት የሚያስተምሩ ነበሩ። ታዲያ አዋሳ ውስጥ 30 ሺ ብር ከካዝና አፍሰው ከቡና ስር መደበቃቸው ተደረሰበት። የገንዘብ ሹሙንና ጸሐፊውን ለማስከፈል በረቀቀ ዘዴ ነበር የሰረቁት።

በወቅቱ የታወቁ ፊውዳል “አገረ ገዥ” ሲዳሞን ይገዙ ነበር። ጉዳዩን ሲሰሙ ለፍ/ቤት ሳያቀርቡ በራሳቸው ስልጣንና ትዕዛዝ በያንዳንዱ ሺህ ብር ልክ 30 ጅራፍ ገርፈው በመላ አገሪቱ የመንግሥት ሥራ እንዳይሰሩ ወስኑባቸው። አጅሬም ያባታቸው ስም ሳህሉ የነበረውን ሳህሌ ብለው ወደ አ.አ. መጥተው ሥራ ይይዛሉ። በሚያውቁት ዘዴ እያምታቱ ይከብራሉ። ብዙ ወዳጅም ያፈራሉ። በመሃሉ ም/ሚኒስትር ተብለው ይሾማሉ። በሳቸው ሞገስ ጥላ ስር የሚኖሩ አሽቃባጮች የደስ ደስ ብለው ከሠራተኛው ህዝብ ገንዘብ ሰብስበው ድግስ ደረጋል። ይበላል፣ ይጠጣል፣ የሰውዬውን ታላቅ ሰውነት እየገለጡ ብዙ እበላባዮች የውዳሴ ንግግር አደረጉ።

ከተጋባዡ አንዱ አቶ እንደልቡን ግን እንዲናገር ሳይጋበዝ መድረኩን በጉልበቱ ይዞ “ዛሬ የምናከብረው በዐል ክቡር አቶ… በመሾማቸው ነው። እኒህ ሰው ደግ፣ ርኅሩህ፣ ጨዋ ተገርፈው ያደጉ ናቸው” ብሎ ሲናገር ቅኔው የገባቸው ሲስቁ አመሹ።

                           ሙሻዘር - ከመርስዔ ኀዘን አበበ

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
82 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 378 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us